በአዲስ አበባ በልመና ላይ የተሰማሩ ሶሪያውያን መመልከት እየተዘወተረ መጥቷል።

በአዲስ አበባ ሰው በሚበዛባቸው እንደ ቦሌ፣ መርካቶ፣ ቄራ እና መስጂዶች በሚገኙባቸው ሌሎች ቦታዎች ባልተለመደ መልኩ በልመና ላይ የተሰማሩ ሶሪያውያን መመልከት እየተዘወተረ መጥቷል። ከሴቶች እስከ ጨቅላ ህጻናት፣ ከወጣት እስከ ጎልማሳ ያሉ ወንድ ሶሪያውያን እርዳታ የሚጠይቁት በአማርኛ የተጻፉ ጽሁፎችን ይዘው ነው።

የኢሚግሬሽን፣ የዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ባለፉት አምስት ወራት 560 ሶሪያውያን በህጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስታውቋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 390ዎቹ ወደ ሃገራቸው መመለሳቸውንም ገልጿል። በኢትዮጵያ ከቀሩት ውስጥ እስካሁን በስደተኝነት በይፋ የተመዘገቡት ግን 96 ብቻ መሆናቸውን የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አስተዳደር ገልጿል።

በህጋዊነት የተመዘገቡትም ይሁን እስካሁን ያልተመዘገቡት ሶርያዊያን ከፍተኛ የሚባል ገንዘብ ወጪ እያደረጉ እንደሚመገቡ እና በህዝብ ሳይሆን በኮንትራት ታክሲዎች እንደሚንቀሳቀሱ የDW ዘጋቢ ታዝቧል። እስከ ሶስት እየሆኑ ለሚከራዩአቸው ቤቶች እስከ 15 ሺህ ብር እንደሚከፍሉም መረጃ አግኝቷል። ሶሪያውያኑ በልመና ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያገኙ እና ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶችም ከሃገሬው የኔ ቢጤ ድጋፍ ፈላጊዎች ይልቅ ለሶርያዊያኑ ከፍተኛ ገንዘብ በቼክ ሳይቀር እንደሚሰጡ ታዛቢዎች ለDW ተናግረዋል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE