የድህረ ምርጫ 1997 ሁከትን ለማጣራት ስለተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን የተወካዮች ምክር ቤት ምላሽ ሰጠ።

የድህረ ምርጫ 1997 ሁከትን ለማጣራት በአዋጅ ቁጥር 478/1998 የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽንን በተመለከተ የቀረበ ጥቆማ ላይ የተሰጠ ምላሽ የ1997 ምርጫ ተከትሎ የተፈጠረውን ሁከት እንዲያጣራ በተቋቋመው ጊዜያዊ ኮሚሽን ሲሰሩ ከነበሩ አባል ጥቆማ ለም/ቤቱ አፈጉባዔ ቀርቦ ነበር፡፡

የቀረበው ጥቆማ በወቅቱ ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጣርቶ በዝርዝር እንዲመረምር ተደርጓል፡፡ ቋሚ ኮሚቴውም ህግና አሰራሩን ተከትሎ የሚከተሉት ድምዳሜዎችና ምክረ ሃሳቦች ላይ ደርሷል፡፡

1. የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ጥቆማው ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንዲቀርብ፣
2. የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እያከናወነ በሚገኘው ተጠርጣሪዎችን ለፍርድ የማቅረብ ሂደት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ በዚሁ አግባብ እንዲታይ ቢደረግ፣
3. በወቅቱ በአዋጅ ቁጥር 478/1998የተቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን በጊዜያዊነት ተቋቁሞ ስራውን ያጠናቀቀና በጊዜው ለነበረው ም/ቤት ሪፖርቱን አቅርቦ ስራውን በማገባደድ ህልውናው ያከተመ በመሆኑ አሁን ላለው ም/ቤት ሪፖርት ሊያቀርብ የሚችልበት የህግ መሰረት የሌለ መሆኑ፣

ስለዚህም ከላይ የተገለፁት ሦስት ነጥቦች ከግምት ገብተው ቀርቦ የነበረው ጥቆማ ምላሽ በዚህ አግባብ የተሰጠ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ታህሳስ 30/2011