በልደተ ክርስቶስ: በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ፍጹም ሰላም ተበሠረ፤ በሰውና በሰው መካከል ያለው ሰላም ግን እክል እያጋጠመው ነው፤ መወያየትና አንድነታችንን መጠበቅ ይገባናል-ቅ/ፓትርያርኩ

የሰላም ጸጋ፣ አምላካዊ ሀብት ቢኾንም፣ በአግባቡ ካልተያዘ በሰዎች ድርጊት ሊወሰድ እንደሚችል ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፤ እኛም በተጨባጭ የምናየው ሐቅ ነው፤ የሀገራችን ሰላም ፈተና እያጋጠመው ያለው፣ በፖሊቲካ ኃይሎች ሽኩቻና አንዱ አንዱን ጥሎ ለማለፍ የሚደረገው ቅድድሞሽ ያስከተለው ችግር እንደኾነ አሌ የማይባል ሐቅ ነው፤ ሁሉም የፖሊቲካ ኀይሎች ሰፊ የውይይት መድረክ በመክፈት በሀገር አንድነትና በሰላም መጠበቅ፣ በዜጎች እኩልነትና ሰብአዊ መብት …

► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE