የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጌድኦ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተማሪዎች መማር አልቻሉም ተባለ

በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ከሚገኙ 320 ትምህርት ቤቶች መካከል የትምህርት ሚንስቴርን መመዘኛ የሚያሟሉት 13ቱ ብቻ እንደኾኑ ዋዜማ ከዞኑ ትምህርት ቢሮ ሰምታለች።

የትምህርት ቤት ግንባታ ጥራት ጉድለት፣ የሰው ኃይልና የቤተመጽሃፍት እጥረትና የትምህርት አመራርና አስተዳደር ጉድለት ዋነኞቹ የዞኑ ትምህርት ቤቶች ችግሮች ናቸው።

በዘንድሮው ዓመት በዞኑ ለመማር ከተመዘገቡት 266 ሺህ 700 ተማሪዎች መካከል፣ ከ18 ሺህ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠዋል ተብሏል።

ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከሚያቋርጡባቸው ምክንያቶች መካከል፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አንዱ እንደኾነ መረዳት ተችሏል።

ምንጭ Link- http://bit.ly/3KdVNGs