በግብፅ ትልቁ ፒራሚድ ውስጥ ግዙፍ የመተላለፊያ ዋሻ ተገኘ

ግብፅ ከምትታወቅባቸው ጥንታዊ ቅርሶች መካከል ጊዛ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በሚገኘው ግዙፍ ፒራሚድ ውስጥ ተሰውሮ የኖረ ግዙፍ መተላለፊያ ዋሻ መገኘቱን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። ዋሻው ዘጠኝ ሜትር ርዝመት ሲኖረው፣ 2.1 ሜትር ደግሞ ስፋት አለው ተብሏል። ይህ መተላለፊያ ዋሻ ምናልባት ወደ ንጉሥ ኩፉ መቃብር ቦታ ሊወስድ ይችላል የሚል ግምት አሳድሯል።…