የአንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝት ፋይዳ ትንታኔ

የዩናይትድ ስቴትሱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝት፤ የሁለቱን ሀገሮች ያለውን ግንኙነት መልሶ ለማደስና ቀድሞ ወደነበረው ደረጃ የመመለስ አንደምታ እንዳለው አንድ ምሑር ተናገሩ።

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምክኒያት የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ሻክሮ ቆቷል የሚል እምነት ያላቸው በኒው ዮርኩ አዮና ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው፤ የብሊንከን ጉብኝ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እንዲያበቃ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ላይ ከተደረገው የሰላም ሥምምነት በኋላ የታየ ለውጥ ነው የሚልም እምነት አላቸው።

ዶ/ር ደረሰ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያና የኒዠር ቆይታቸውን አጠናቀው የተመለሱትን የዩናይትድ ስቴትሱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ ጉብኝት ፋይዳ በተመለከተ ትንታኔ ሰጥተውናል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።