በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ላይ ጫማ የወረወረው ኢራቃዊ ያለበት ሁኔታ

በፈረንጆቹ 2008 የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ በኢራቅ መዲና ባግዳድ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ እያሉ ነበር ጫማ የተወረወረባቸው። ጫማ የወረወረባቸው ኢራቃዊ ጋዜጠኛ ሙንታዜር አል-ዛይዲ ወዲያውኑ የዓለም መነጋገሪያ ሆኖ፣ በአሜሪካ ወረራ የተበሳጩ ኢራቃውያን ደግሞ ጀግናቸው መሆኑን አደባባይ ወጥተው ገልጸው ነበር። በወቅቱ ይህንን ያደረገው የአሜሪካ መራሹ ወረራ በአገሩ ላይ ያመ…