ሰርጂዮ ራሞስ፡ ጫማ መስቀል አሻፈረኝ ያለው ቱጃሩ እግር ኳሰኛ፤ መጨረሻው የት ይሆን?

የዓለም ዋንጫ፣ የአውሮፓ ዋንጫ፣ አራት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ፣ አምስት ጊዜ ላ ሊጋ፣ አንድ የሊግ ዋንጫ ያነሳው የ36 ዓመቱ ስፔናዊ ተከላካይ። ብዙዎች ይህን ድል ቢያገኙ ጫማቸውን ሰቅለው ስፋቱ ፈረስ በሚያስጋልብ ቤት ተንደላቀው ጡረታቸውን ያጣጥሙ ነበር።…