እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ድሐ አገሮችን ሮሮ ማን ይሰማል?

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት “በትንሹ ያደጉ” የሚባሉ 46 ደሐ አገሮች ጉባኤ በቃጣር በመካሔድ ላይ ይገኛል። የድሆቹ አገራት መሪዎች እና ባለሥልጣናት በቃጣሩ ስብሰባ ሮሯቸውን እያሰሙ ነው። ይኸ ቡድን ከተመሠረተ አምስት አስርት ዓመታት ቢሻገርም ይኸ ነው የሚባል ለውጥ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ነዋሪዎች ላሏቸው አገራት አልታየም።…