በኢትዮጵያ ውስጥ አንዱ ገዳይ ግጭት መረጋጋት ሲጀምር፣ ሌላው ደግሞ እያደገ ነው፣ ይህም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ማዕቀቡን እንዲያነሳ ለማሳመን እና በአንድ ወቅት በአፍሪካ ፈጣን ኢኮኖሚ እያስመዘገቡ ካሉት አገሮች መካከል አንዱ የነበረውን እንደገና ለማነቃቃት የሚጓጓውን መንግስት እየፈታተነ ነው።የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው ወር በመንግስታቸው እና በሀገሪቱ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለማስተዋወቅ በዚህ ሳምንት የአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በተገኙበት ወቅት እንኳን፣ ትልቁ የኦሮሚያ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ ያልተረጋጋ ከመሆኑም በላይ ጦርነቱ ብሶበስ ሰላማዊ ዜጎች እያለቁ ነው።
በአፍሪካ ሁለተኛዋ በሕዝብ ብዛት 120 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት አገር፣ በጎሳ ቡድኖች እና በታጠቁ አጋሮቻቸው መካከል ከሞት የሚያደርስ ውጥረት ጋር እንደገና እየታገለች ነው። በሀገሪቱ ትልቁ የሆኑት የኦሮሞ እና የአማራ ብሄረሰቦች ግድያ ከመጠን በላይ አድጎ ከፍተኛ ቁጥሩን ይዞታል። እጅግ አሰቃቂ ነው። የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ብዙ ጊዜ ስለሚቋረጥ እና ነዋሪዎቹ ብዙ ጊዜ የሚናገሩ ከሆነ አጸፋውን በመፍራት በኦሮሚያ በተፈጠረው ሁከት የሟቾች ቁጥር አይታወቅም። እስካሁን የተመዘገቡ በመቶ ሺሆን የሚቆተሩ አማሮች አልቀዋል።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይገለጽ ያልፈለጉ አሶሼትድ ፕሬስ ያነጋገራቸው በርካታ የኦሮሚያ ነዋሪዎች ባለፉት ሳምንታት የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት ገልጸዋል። በክልሉ ኪራሙ ወረዳ አንድ እማኝ ከህዳር 24 ጀምሮ ከተገደሉት ቢያንስ 34 ሰዎች መካከል አባቱ እና የአጎታቸው ልጅ መሆናቸውን ተናግሯል። ገዳዮቹ የመንግስት ሰዎች ናቸው ያለው እማኝ በኦሮሚያ ክልል መንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ወታደሮችን ዩኒፎርማቸውን አይቻለሁ ሲል ወቅሷል።
“ይህ ሁሉ የተጀመረው በአንድ የአካባቢ ሚሊሻ እና በኦሮሚያ ልዩ ሃይል አባላት መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው” ብሏል። “ልዩ ሃይሉ የአማራ ማህበረሰብ አባል የሆኑትን ሚሊሻዎች ገድሏል፣ከዚያም ለአንድ ሳምንት የፈጀ ግድያ ተከተለ።” ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አካባቢውን ለቀው መሰደዳቸውን ገልጿል። ሲል አሶሴትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የኪራሙ ከተማ ነዋሪ የሆነ የኦሮሞ ተወላጅ ግን ፋኖ ተብሎ የሚጠራው የአማራ ታጣቂ ቡድን በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እና ግድያ ፈጽሟል ሲል ከሷል እና ከ12 በላይ አስከሬኖችን አይቶ አራቱን የቀበረው ህዳር 29 ነው። “ይህ የሚሊሺያ ቡድን ህዝባችንን እየገደለ፣ መንደሮችን እያቃጠለ እና ያለንን ሁሉ እየዘረፈ ነው” ሲል ዱጋሳ ፈይሳ ለአሶሴትድ ፕሬስ ተናግሯል። “በሚያገኙት ሰው ላይ ይተኩሳሉ…የህዝብ አገልጋዮች፣ፖሊስ መኮንኖች ወይም አስተማሪዎች ይሁኑ።” ብሏል። ኦሮሞ እና አማራ አብረው ኖረዋል ለዓመታት ኖረዋል ነገርግን ከዚህ በፊት እንዲህ ሲጣሉ አይተው እንደማያውቅ ተናግሯል።
ባለፉት ሳምንታት በኦሮሚያ ተከስቶ የነበረውን አስከፊ ሁከት የተመለከተ የጊዳ አያና ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪም የአማራ ፋኖ ተዋጊዎችን ተጠያቂ አድርገዋል። ፋኖ ይሁኑ አይሁኑ ከነፃ ወገን የተሰተ ማረጋገጫ የለም።
“በአካባቢያችን ያሉ ዜጎች እየተገደሉ፣ እየተፈናቀሉና እየተዘረፉ ነው። ይህ ቡድን በጣም የታጠቀ በመሆኑ መከላከያ ለሌላቸው አርሶ አደሮች አይመጣጠንም” ያሉት አቶ ጌታሁን ቶሌራ በአሁኑ ወቅት በአቅራቢያው ከሚገኙ ወረዳዎች የተሰደዱ 31,000 ያህል ሰዎችን ያስተናግዳል ብለዋል። አሁንም ከቤት ወደ ቤት እየሄድን አስከሬን እያገኘን ነው።
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ስለተፈጸሙት ግድያዎች አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተው እስካሁንም በግልፅ አልተናገሩም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሳምንት እንዳሉት ዝርዝር መግለጫ ሳይሰጡ አንዳንድ “ጽንፈኛ አመለካከት ያላቸው ጠላቶች” አገሪቱን ለማተራመስ እየሞከሩ ነው። ማለታቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች፣ የኦሮሞ ታጣቂዎች እና የአማራ ሚሊሻዎች በኦሮሚያ፣ በኢትዮጵያ ትልቁ ክልል እርስ በርስ እየተዋጉ መሆኑን የአለም አቀፍ ቀውስ ግሩፕ ተንታኝ ዊሊያም ዴቪሰን ተናግረዋል።”መንግስት ከአማፂያኑ ጋር እየተጠናከረ ባለበት ወቅት ሦስቱም በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን በተለይም የአማራ ተወላጆችን በማጥቃት ህብረተሰባቸውን እንከላከላለን የሚሉ የአማራ ታጣቂዎች ጥቃት እንዲጨምር አድርጓል” ብሏል።