ሸህ መሐመድ ሁሴን አል አልአሙዲ በህይዎት አሉ !

ሸህ መሐመድ ሁሴን አል አልአሙዲ በህይዎት አሉ !
=============================
* ሳውዲው ባለስልጣ ክስ እንደተመሰረተባቸው ተናግረዋል
* አፈ ቃላጤያቸው ግን ክስ መመስረቱን አስተባብሏል

ባሳለፍነው ወር ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሳውዲ ዜጋ የሆኑት አለም አቀፉ ባለሀብት ሸህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ ” ከእስር ተፈተዋል ” በሚል ሀሰተኛ መረጃ ተሰራጭቶ ተመልክተናል ። ከዚያም ወዲህ ሸሁ በህይዎት እንደሌሉ በሰፊው ሲነገር መሰንበቱ ይታወሳል ። ነገር ግን አሁንም በሸህ ሁሴን መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ የተሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን ታውቋል ።

ከሁለት ቀናት በፊት ይፋ የሆነው አንድ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን እንዳሳዎቀው ባለፉት አንድ አመት በሳዑዲ አረቢያ መንግስት በቁጥጥር ስር የሚገኙ ሸህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲ በህይዎት መኖራቸውን ጠቁሟል ። ሸህ አል አሙዲ በሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በቅርቡ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የሳውዲ መንግስት ባለስልጣን ብሎምበርግ ተብሎ ለሚጠራው የዜና አውታር አስረግጠው ተናግረዋል ።

የዜና አውታሩ ይን ይበል እንጅ የሸህ አሙዲ አፈ ቀላጤ ፔንድሪ Tim Pendry በበኩላቸው ሸሁ በምንም አይነት ወንጀል ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ከመግለጽ ባለፈ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ መንግስት ሸሁን ለማስፈታት አሁንም የሳውዲ መንግስትን በመወትወት ላይ ሰለመሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ !

እስኪ ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ታህሳስ 7 ቀን 2011 ዓም

https://www.bloomberg.com/…/saudi-ethiopian-billionaire…