ሼክ መሐመድ አልአሙዲ በሳዑዲ አረቢያ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው።

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የሚገኙት ሼክ መሐመድ አል-አሙዲ የሙስናና ጉቦ ክሶች እንደቀረቡባቸው እና በቅርቡ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ አንድ የሳዑዲ አረቢያ ባለሥልጣን ተናገሩ።

ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ የሳዑዲ ባለሥልጣን አል-አሙዲ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ የሚችሉበት ቀን ገና አለመታወቁን ተናግረዋል። አል-አሙዲ በሳዑዲ አረቢያው ልዑል መሐመድ ቢን ሰልማን በተጀመረው ፀረ ሙስና ዘመቻ ከሌሎች የሳዉዲ ቢሊየነሮች እና ከፍተኛ የንግድ ሰዎች ጋር ከታሰሩ ከአንድ አመት በላይ ሆኗቸዋል።

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት የሳውዲ ባለስልጣን አላ ሙዲ በእስር ላይ እንዳሉ ሕይወታቸው አልፏል በሚል የሚናፈሰውን ዜናም አስተባብለዋል። የአላ ሙዲ ጠበቃ ቲም ፔንድሪ በበኩላቸው ክስ ቀርቦባቸዋል የሚለውን አጣጥለዋል።

DW