የአማራ ክልል ነዋሪ መሆን ወንጀልና ነውር የሆነ ይመስል .!!!!! #ግርማካሳ

ከትግራይ ዛላምበሳ ወደ ኤርትራ ሰንዓፈ ማለፍ አስቸጋሪ እንደሆነው፣ ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ ማለፍም አስቸጋሪ የሆነበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡ በትግራይና በኤርትራ መካከል ችግር ቢኖር በጦርነቱ ምክንያት ነው፡፡ በመሃል ሸዋ ግን በጦርነት ምክንያት አይደለም፡፡

ታዲያ ምንድን ነው ችግሩ ? ዜጎች በሰላም አገር ከደብረ ብርሃን ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የሚከለከሉት በምን ምክንያት ነው ?በኔ እይታ አራት ምክንያት ያሉ ይመስለኛል፡፡

1ኛ የዘመኑ ሰዎች ጡንቻቸውን ለማሳየትና ምን ታመጣላችሁ ለማለት ስለፈለጉ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

2ኛ ሌላው ማህበረሰብ መብቱ ሲገፈፍና ሲሰቃይ ከማለቃቀስ ውጭ መብቱን ለማስክበር የተዘጋጀ ባለመሆኑ ነው፡፡ ባርነት፣ ግፍን፣ ጭቆናን አሜን ብሎ በመቀበሉ፡፡

3ኛ ባለተረኞች የአማራ ማህበረሰብ አባላት በአዲስ አበባ እየበዙ ናቸው ከሚል፣ ከአማራ ክልል ፍልሰቱን ማስቆም አለብን ከሚል ነው፡፡

4ኛ ትልቁ ምክንያት ደግሞ ሌብነት ነው፡፡ እንደ እሮሞ ክልል ሃላፊዎችና ፖሊሶች ሌባና ዘራፊ፣ ጉቦኛ የለም፡፡

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት፡፡ ከሁሉም የአገሪቷ ግዛት ኢትዮጵያዉያን ወደ ዋና ከተማቸው የመምጣት፣ በዚያም የፌዴራል መንግስትን አገልግሎቶች የማግኘት መብት አላቸው፡፡ በአዲስ አበባ በተለያዩ ጉዳዮች ዜጎች ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ፡፡ ዘመድ ለመጠየቅ ለህክምና ፣ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ውጭ አገር ለመውጣት፣ በአዲስ አበባ ቢዝነሶች ለመከፈት ወዘተ …። ግን ተረኞች ለዚያ ደንታ የላቸውም፡፡ ፍጹም ጋሪዪሻዊና ዘረኛ ገጽታቸውን እያሳዩ ነው፡፡

በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው የኦሮሞ ክልል ፖሊሶች፣ በፖለቲካ አመራሩ መመሪያ መሰረት፣ ዜጎችን እያስቆሙ፣ መታወቂያ እያዩ፣ አማራ ክልል ነዋሪ መሆን ወንጀልና ነውር የሆነ ይመስል፣ የአማራ ክልል ነዋሪዎችን ወደ አዲስ አበባ በእንዳይገቡ ማገዳቸው ነው፡፡

ሰዎቹ በአዲስ አበባ እያደረጉት ያለው መረን የለሽ ተረኝነትና ዘረኝነት አልበቃ ብሏቸው፣ በዚህ መልኩ፣ በጅምላ የአማራ ክልል ሕዝብ ወደ ከተማው እንዳይገባ ማድረጋቸው ፣ በሕዝቡ ላይ በይፋ ጦርነት ከማወጅ ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡

የአማራ ክልልን እንወክላለን የሚሉ የአማራ ብልጽግና ሰዎች ወዴት ነው ያሉት ? የሚለው ሌላው ትልቁ ጥያቄ ነው፡፡ በአማራ ክልል ህዝብ ላይ፣ ይሄ ሁሉ ያፈጠጠ፣ አይን ያወጣ፣ አስነዋሪና ዘረኛ ተግባራት፣ በአብይ አህመድ የኦህዴድ አገዛዝ ሲፈጸሙ፣ እንዴት “ለምን” ማለት ይሳናቸዋል ??? ምን አልባት እነርሱ ወደ አዲስ አበባ ያለምንም ችግር በአይሮፕላን መውጣት መግባት ይችሉ ይሆናል፡፡ ግን ሌላው ቢቀር ትንሽ እንኳን ለመጡበት ማህበረሰብ መቆርቆር እንዴት ይሳናቸዋል ???? ምን አይነት ሞራለቢስነትና እርግማን ነው የተጠናወታቸው ????