ለምግብ አለመፈጨት የሚያጋልጡ ልምዶች አና መፍትሄዎች

ለምግብ አለመፈጨት የሚያጋልጡ ልምዶች አና መፍትሄዎች
‹‹እየሰሩ መመገብ ለምግብ አለመፈጨት ያጋልጣል፡፡››
የስነ ምግብ ባለሙያ

የምግብ አለመፈጨት ችግር በብዙ ሰዎች ዘንድ እየተለመደ የመጣ የጤና እክል ሆኗል ይላሉ፡፡ ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም፣ የጨጓራ ህመም እና ሌሎች የስቃይ ስሜቶች የሚስተዋሉ ምልክቶች ናቸው፡፡ እንግሊዛዊቷ የስነ-ምግብ ተመራማሪ ማርታ ኢንሄሉሽ የምግብ አለመፈጨት ምክንያት ያለቻቸውን የኑሮ ዘይቤዎች እና ልምዶችን ይፋ አድርጋለች፡፡

የምግብ መፈጨትን በዋናነት የሚያካሂደው የአሲድ መጠን ዝቅትኛነት ምግብ በአግባቡ እንዳይፈጭ ያደርጋል፡፡በተቃራኒው ከፍተኛ የአሲድ መጠን የምግብ አለመፈጨት ችግር ያስከትላል ተብሎ ይታሰብ እንደነበር ማርታ አሳውቀዋል፡፡ ለዚህም ይህን አሲድ እንዲመነጭ የሚያደርጉ ምግቦቸን መመገብ ተገቢ ነው፡፡

እየሰሩ መመገብ ሌላው ምክንያት ነው፡፡ እየተመገብን በስራ ስንወጠር አዕምሯችን የምግብ መፈጨት እንዲካሄድ ትዕዛዝ ለመስጠት ይቸገራል፡፡ በመሆኑም ስራ እየሰራን የመመገብ ልምድን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ከፍተኛ ቅባት ያላቸውን እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን በብዛት መመገብ የምግብ አለመፈጨት ሌላው ምክንያት ነው፡፡በነዚህ የምግብ አይነቶች ውስጥ አብላይ ባክቴሪያ አለ፡፡ ይህም በትንሹ አንጀት ውስጥ ጋዝ እንዲፈጠር እና ምግብ በአግባቡ እዳይፈጭ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪ ውሀ አብዝቶ መጠጣት፣ ከተለመደው ሰዓት ዘግይቶ መመገብ፣ የቁርስ፣ ምሳ እና እራት የመመገቢያ ሰዓትን አለማራራቅ፣ በስርዓት አለማኘክ፣ ከፍተኛ የሥኳር መጠን ያላቸውን የአልኮል መጠጦች መውሰድ (ኮክቴል፣ወይን) እና ሌሎች ምክንያቶች የምግብ አለመፈጨት ችግር እንደሚያስከትሉ ማርታ ጠቁመዋል፡፡ በመፍትሄነት ከቀረቡት መካከል የየቀኑን የቁርስ፣ ምሳ እና እራት መመገቢያ ሰዓት ተመሳሳይ ማድረግ፣ ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ፣ በየቀኑ 10 ሺህ ርምጃዎች ያክል በእግር መጓዝ፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን ማዘውተር እና በየአንድ ሰዓት ልዩነት ከመቀመጫ ተነስቶ መንቀሳቀስ ተጠቅሰዋል ይላል ዴይሊ ሜል በዘገባው፡፡

ምንጭ፡-ዴይሊ ሜል
በቢኒያም መስፍን