የፌዴራል ፖሊሶች ባሕርዳር ላይ በዋስ የተፈቱትን የሸዋ ፋኖዎች ወደ አዲስ አበባ ይዘን ካልሄድን በሚል ግብግብ መፈፀማቸውን ቀጥለዋል

የሸዋ ፋኖ አመራሮችንና የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች አባላትን አሁን የባህር ዳሩ የክልሉ ፍ/ቤት በዋስ እንዲፈቱ ቢፈቅድም ከፌደራል ተልከን የመጣን ነን ብለው ወደ አዲስ አበባ ይዘን እንሔዳለን ብለው ግብ ግብ እየፈጠሩ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀውልናል።

በሸዋ ፋኖ አመራሮች ላይ እየተደረገ ያለው ማወከብ ይቁም!!

ሃገር ምጥ በተያዘች ጊዜ ከህዝባቸው ጋር ተሰልፈው ጠላትን የተፋለሙ ጀግኖች ናቸው።

በሸዋ ፋኖ አመራሮች ላይ የተካሄደው አፈናና ዕስር በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

ህዝብን አስተባብሮ የሃገርን ክብር ያላስደፈሩ ወጣቶችን በማሰር የሚካሄድ ምንም የሚመጣ ለውጥ የለም።

በሸዋ ፋኖ አመራሮች ላይ እየተካሄደ ያለው መንግስታዊ ዕስር ፓለቲካዊ ከመሆኑ ባሻገር ሸዋን በአሸባሪ ሃይሎች ወረራ እንዲካሄድበት ማመቻመች መሆኑ የቅርብ ጊዜውን ጭፍጨፋ ለማየት በቅተናል።

በዛሬው ዕለት በባ/ዳር ከተማ ችሎት የተደረገ ሲሆን በችሎቱም የሸዋ ፋኖ አመራሮች ጉዳያቸውን ወደ ፌደራል እንዲሄድ መወሰኑ በፍፁም ተቀባይነት የለውም።

የተያዙበት እና እየተዳኙበት ያለው ክልል እያለ ለፌደራል መንግስት ተላልፎ ይሂዲስ ማለት መጨረሻው ምን ይሆን??

በህግ ማስከበር ስም እየተደረገ ያለው ፀረ ፋኖ እንቅስቃሴ የክልሉን ህዝብ ሆነ መንግስትን አይጠቅመውም።

የአማራን ህዝብ በአዲስ መልክ በመደበኛ፣ኢ-መደበኛ ባልሆነና በኢ-መደበኛ መንገድ ማዳራጄት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው።

ከዚህ ውጭ ህዝብን ሃገርን እየበዘበዙ ለጥሬ ስልጣን ፈላጊዎች ግብአት መሆን ተገቢነት ያለው አካሄዲ አይደለም።

የሸዋ ፋኖ አመራሮች ህዝባቸውን ከማደራጀት ውጭ ወንጀል አልሰሩም።
እየተካሄደባቸው ያለው አፈናና ዕስርም ፓለቲካዊ አንድምታ ያለው ነው።

ይሄን በስርዓት እና በመዋቅር ስር ሆኖ የነቁ ሰዎችን ማሰር፣ማዋከብ እና መግደል ፋሺን አድርጎ መቀጠል ዳግማዊ ወያኔነት ነው።

ህዝብን በዘር ለይቶ የሚያጠቃ ስርዓት በተፈጠረበት ሃገር ውስጥ የአማራ ፋኖ አደራጆች ላይ የሚደረገው ፀረ ፋኖ ውንጀላ የብልፅግና ስርዓትን ዕድሜ ያሳጥራዋል እንጅ አይጠቅመውም።

ሃገርን በጠራራ ፀሃይ እያስወረሩ፣እያዘረፉ እና ሉአላዊነቷን ጭምር እያስደፈሩ ፋኖ ላይ ብቻ የቀውስ ፓለቲካ መጠመቅ ወንጀል ነው።