በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ውስጥ የሚፈፀመው አሻጥር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል

በኢትዮጵያ_ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ውስጥ የሚፈፀመው አሻጥር ትኩረት ሊሰጠው ይገባል!!

በነገራችን ላይ አዲሱ አመራር ከመጣ ወዲህ የተለያዩ ለውጦችን በሀገራችን ላይ አይተናል ፡፡ ይህም ለውጥ ይበል የሚያሰኝ እና የሚያስደስት ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ድርጅቶች ዙሪያ የሚፈፀሙ የመልካም አስተዳደር እና የሙስና ጥፋቶች ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር ለመጣው ለውጥ እንቅፋት ሊሆን ስለሚችል ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ውስጥ ህግ ወጥ አሰራር እየሰፋ የህዝብ ገንዘብ እየተመዘበረ በመሆኑ ለሚመለከተው ክፍል እንድታሳውቅልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ለዚህም መገለጫው በተለይ በድርጅቱ የሚገኘው የሥራ ኃላፊ ከድርጅቱ ሥራ ከቀረ እና ሥራ እንዲበደል ካደረገ የሰነበተ ሲሆን የራሱን ጀሌዎች በመሰብሰብ የድርጅቱ የዞን ቢሮዎች ከሆኑት ከአሠላ፣ አርባምንጭ፣ ሐረር እና ድሬዳዋ ቢሮዎች ከሚገኙ ኃላፊዎች ጋር ያልተገባ ግንኙነት በማድረግ ዘረፋውን ያጠናከረ ከመሆኑም ባሻገር በቅርቡም እንዳበደ ሰው ሆኖ የድርጅቱ ሰርቨር ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ወንጀለኛ በቀላሉ አንድ ቀን ብቻ አራዳ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያድር ተደርጎ ከህግ ተጠያቂነት እንዲያመልጥ ተደርጓል፡፡

በድርጅቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ከሚገለፅባቸው ጉዳዮች አንዱ ያለብቃታቸው የተመደቡ እና በድርጅቱ አመራር ውስጥ ከ40-60 በመቶ መቀመጫ የያዙት የአንድ አካባቢ ብሄር ተወላጆች ጉዳይ በአንድ ወቅት የስልሳ ሺህ ዜጎች የደም ዋጋችን ተብሎ ሲፎከርበት የቆየ ቢሆንም አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን ትኩረት ያላገኘ መሆኑን እና ድርጅቱን አደጋ ውስጥ የከተተ ጉዳይ መሆኑን መደበቅ አይሻም፡፡ ይህንን ስንል ይህንን አንጋፋ የህዝብ ተቋም ለመታደግ እንጂ እንደኛው ደክመው ጥረው ግረው የሚኖሩትን የድርጅታችንን የትግራይ ብሄር ተወለጆችን በጥላቻ ፖለቲክስ ገፍትሮ ለመጣል አይደለም፡፡

በተጨማሪም ከዚህ በፊት ሲጠቀስ ከነበሩት የዝርፊያ ወንጀሎች ባሻገር የድርጅቱ ሂሳብ ተጠናቆ እንዳይታወቅ በአግባቡ ኦዲት እናዳይደረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
እባክህ የህዝብ ድርጅት የሆነውን ፖስታ ቤት እንዳይወድቅ እንታደገው!!! ለደህነታችን ሲባል ስማችንን ባለመጥቀስ ተባበረን፡፡ ድምፃችንን አሰማልን>>