ሕገወጥ 64 ሺህ 50 ዶላርና 56 ሽጉጦች ተያዘ

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 64 ሺህ 50 ዶላርና 56 ሽጉጦች መያዙን የገቢዎች ሚኒስተር አስታወቀ ።

64 ሺህ 50 ዶላሩ ከአንዲት ተጠርጣሪ በቶጎ ውጫሌ በኩል ከአገር ሊወጣ ሲል በጉምሩክ ኬላ መያዙን ገልፆ 56 ሽጉጦችን ደግሞ አርበረከቴ በተባለ ቦታ ሁለት ግለሰቦች በመኪና ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል።