የክልል ፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር ነው

በደቡብ ክልል የሚነሱ የክልል ፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር ነው

በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል የሚነሱ የክልል፣የዞን እና የልዩ ወረዳ ጥያቄዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመመለስ የሚያስችል ጥናት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ።

ጥናቱ የሚጀመረውም የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባለፈው መስከረም ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እየተነሱ ያሉት ጥያቄዎች ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንዲፈቱ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት መሆኑ ነው የተገለፀው።

በዚህ መሰረትም ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችለውን ጥናት ለማካሄድ ከምሁራን፣ከወጣቶች እና ከመንግስት ሰራተኞች የተውጣጡ 20 አባላትን የያዘ ኮሚቴ መቋቋሙን የጥናት ቡድኑ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ዶክተር ያኒአ ሰይድ መክይ ተናግረዋል።