የጅማ – አጋሮ – ዲዴሳ ወንዝ ድልድይ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ጠ/ሚ ዓብይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተጀመረ።

የጅማ – አጋሮ – ዲዴሳ ወንዝ ድልድይ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በተገኙበት በይፋ ተጀመረ።


የአንድን ሀገር ልማት በማፋጠን ረገድ ጉልህ ሚና ካላቸው የመሰረተ ልማት ዘርፎች አንዱ መንገድ ነው፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እና በነደፈው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት የዘርፉ ዋነኛ ባለቤት የሆነው የመንገዶች ባለስልጣን ለተግባራዊ እንቅሰቃሴው ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የጅማ – አጋሮ – ዲዴሳ ወንዝ ድልድይ የመንገድ ፕሮጀክት ነባሩ መንገድ ገፅታ
• በጠባብ የአስፋልት መንገድ ደረጃ የነበረ
• የ50 ዓመት አገልግሎት የሰጠ
• በ5 ሜትር ስፋት እጅግ አስቸጋሪ የነበረው እና
• ለትራፊክ እንቅስቃሴዎች ምቹ ባለመሆኑ ለአደጋ ሲያጋለጥ የነበረ መንገድ ነው፡፡
የጅማ – አጋሮ – ዲዴሣ ወንዝ ድልድይ የመንገድ ፕሮጀክት አዲሱ መንገድ ገፅታ
• የ2ኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር አንድ አካል ነው፡፡
• የአገሪቱን ደቡብ አና ሰሜን ምዕራብ ክፍሎች ደረጃውን በጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት ያስተሳስራል፡፡

መገኛ ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት – ጅማ ዞን ጅማ ከአዲስ አበባ ምዕራባዊ – ደቡብ አቅጣጫ ወሊሶን አቋርጦ በሚያልፈው አስፋልት ኮንክሪት መንገድ 360 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት።
መነሻ እና መድረሻ ፕሮጀክቱ የሚጀመረው ጅማ ከተማ ከሚገኘው “ሃኒላንድ” ሆቴል በመነሳት በዋናነት በጅማ ሰሜን – ምዕራብ አቅጣጫ አድርጐ ወደ አጋሮ እና ዴዴሣ ወንዝ ድልድይ ድረስ የሚዘልቅ ነው፡፡ ከዚያም ከወንዙ እስከ መቱ ከተማ በሚዘልቀው በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኘው መንገድ ጋር ያገናኛል፡፡

ኮንትራት እና ውል
የሥራ ተቋራጭ ቻይና ሬል ዌይ 21ኛ ቢሮ ግሩፕ የተባለ አለም አቀፍ ድርጅት
አማካሪ ድርጅት ኦሜጋ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ እና ፕሮሜ ኮንሰልታንትስ በጋራ
የግንባታ ወጪ ከ1.3 ቢሊዩን ብር በላይ
የግንባታ ጊዜ 41 ወራት
የግንባታ ወጪ ሽፋን የኢትዮጵያ መንግስት ነው።

አዲሱ መንገድ
አጠቃላይ ይዘት ወደ አስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲያድግ ተደርጐ ይገነባል፡፡
ርዝመት 79.07 ኪ.ሜ.
ስፋት በከተሞች የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 22.5 ሜ. እንዲሁም በገጠር የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 7.10 ሜ.
የአገልግሎት ሽፋን ጅማ ዞን ውስጥ የሚገኙ ወረዳዎችን / ማና፣ ጎማ፣ ጉማይ/ ያገናኛል በተጨማሪም ከቡኖ በደሌ ዞን ጋር ያስተሳስሪል
የሚያካትታቸው ሥራዎች
• ነባሩን መንገድ ማስፋት
• የአስፋልት ኮንክሪት ሥራ
• ነባሩን መንገድ ጥገና በማካሄድ /ለትራፊክ እንቅስቃሴ ምቹ እየተደረገ / የደረጃ ማሻሻያ ሥራ ማከናወን
• የአፈር ቆረጣና ሙሌት
• የአቃፊ /መከላከያ ግንብ ሥራ
• የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች ግንባታ ሥራ
• ነባሩን የዴዴሳ ወንዝ ድልድይ መጠገን ፣ ማጠናከር
• ትልልቅና አነስተኛ የውሃ መተላለፊያ /መፍሰሻ
• ቱቦዎች ሥራ
• እና በርካታ የስትራክቸር ሥራዎች ናቸው፡፡

የፕሮጀክቱ ሁለንተናዊ ፋይዳ
• ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል
• የተሽከርካሪ የጉዞ ወጪና ጊዜ ይቀንሳል
• የምርት እና የሸቀጥ ልውውጥን ያቀላጥፋል
• የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ በማውጣት የገበያ ተደራሽነትን ያቀላጥፋል
• የከተሞች የእርስ በርስ ትስስር ይፈጥራል
• የጤና ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ተደራሽነት ያጠናክራል
• የማህበረሰቡን ኑሮና በኢኮኖሚው ዕድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል
• ቡናን ጨምሮ በግብርና ምርቶችና በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገውን አካባቢ ተጠቃሚ ያደርጋል ።
( መንገዶች ባለስልጣን )