ሰፋ ያለ አመለካከትን፤ እርቅን፤ አንድነትን፤ እና ትብብርን ማቀንቀን አስፈላጊ ነው = ( ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ )

ሰፋ ያለ አመለካከትን፤ እርቅን፤ አንድነትን፤ እና ትብብርን ማቀንቀን አስፈላጊ ነው = ( ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ )

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 13ኛውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን በማስመልከት በዘሬው ዕለት ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ 140 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎችን በጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ተቀብለው አነጋገሩ።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ከተማሪዎቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ ከመገለልና ልዩነትን ከማቀንቀን ይልቅ ሰፋ ያለ አመለካከትን፤ የእርቅን፤ የአንድነትን፤ እና የትብብርን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የራሳቸው ጥበብ፤ ቋንቋ፤ ማንነት፤ እና አገር በቀል ዕውቀት ባለቤት መሆናቸውን ከግምት ማስገባት ታላቅ ትምህርት እና ግንዛቤ ለመውሰድ እድል ይሰጣል ብለዋል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE