ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከአውሮፓ የቀውስ ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጋር መወያየታቸው ተገለፀ

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከአውሮፓ የቀውስ ሥራ አመራር ኮሚሽነር ጄኔዝ ሌናርሲች ጋር መወያየታቸው ተገለፀ

ዣኔዝ ሌናርቺች ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ ከተማ በማቅናት ከዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መክረዋል።

የአውሮፓ ህብረት (EU) የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ትላንትና በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ከመከሩ በኃላ ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው ክልሉን ከሚያስተዳድሩት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር መክረዋል።

በውይይቱ የተለያዩ የጋራ ጉዳዮች መነሳታቸውን ከሚገልፅ መረጃ ውጭ ዝርዝር ነገር አልተገለፀም።

ኮሚሽነሩ ከውይይቱ ቀደም ብሎ የዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል መጎብኘታቸውን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል።

ኮሚሽነር ጄኔዝ ሌናርሲች ቀደም ብለው በመቀለ ከተማ የሚገኘውን የአይደር ሆስፒታል መጎብኘታቸውንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።