13ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓልን በማስመልከት በመስቀል አደባባይ የቡና ጠጡ ስነ ስርዓት ተከናወነ

10 ሺህ ሰዎች የታደሙበት የቡና ጠጡ ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው

በአዲስ አበባ የሚከበረውን 13ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በዓልን በማስመልከት በመስቀል አደባባይ የቡና ጠጡ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሀብት የሆነውን ቡናን ለማስተዋወቅ ዓላማ ባደረገው የቡና ጠጡ ስነ ስርዓቱ ላይም 10 ሺህ ሰዎች እየታደሙበት ይገኛሉ።

የቡና ጠጡ ስነ ስርዓቱም “ኑ ለሰላም ቡና እንጠጣ” በሚል መሪ መልዕክት ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።

የቡና ጠጡ ስነ ስርዓቱ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡ የብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች እና የከተማዋ ነዋሪዎችም እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

10 ሺህ ሰው እየተሳተፈበት የሚገኘውን የቡና ማፍላት ሥነ-ሥርዓቱን በጊነስ ወርልድ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ ላይ ለማስመዝገብ ጥረት እንደሚደረግም ታውቋል።