በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ከ10 የሚበልጡ የኦሮሞ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ምክክር ጀመሩ።

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ከ10 የሚበልጡ የኦሮሞ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ምክክር ጀመሩ።

የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅም ለማስከበር በተናጠል የሚንቀሳቀሱት የፖለቲካ የሚቀራረቡባቸውን ሀሳቦች በማስቀደም በጋራ አንድ ጠንካራ ፓርቲ ሊመሰርቱ የሚስችሉበትን ሁኔታ መፈተሽ እና የኦሮሞ ሕዝብ ቀጣይ የትግል ምዕራፍ አቅጣጫም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ኦሮሚያን የሚያስተዳድረው የኦሮሞ ዴሞክራስያዊ ኦዴፓን ጨምሮ ሌሎች 13 ፓርቲዎች፣ እንዲሁም፣ አባ ገዳዎችና የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና የመብት ተሟጋቾች ተሳታፊዎች ናቸው።

DW Amharic


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE