ተከስቶ የነበረው የቤንዚን እጥረት እየተቃለለ ነው ተባለ

ተከስቶ የነበረው የቤንዚን እጥረት እየተቃለለ ነው፡- የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢዎች

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት እንደገለፀው የቤንዚን እጥረቱ እየተቃለለ የመጣው የሚመለከታቸው አካላት የተቀናጀ ጥረት በማድረግ ለእጥረቱ መንስኤ የነበረውን ህገወጥ ንግድ ለመቆጣጠር ጥረት በማድረጋቸው ነው።

እጥረቱ የተከሰተው በህገወጥ መልኩ ከነዳጅ ማደያ ውጪ ቤንዚንን በበርሜልና በጀሪካን የመሸጥ ተግባር በበርከታ አካባቢዎች እየበዛ በመምጠቱ እንደነበር ድርጅቱ እስታውቋል።

አሁንም እጥረቱን ሙሉ በሙሉ ለመፍታት ከንግድ ቢሮዎች ከፖሊስ እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት የተውጣጣ ኮሚቴ የጀመረውን ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያጠናክርም ተገልጿል።

ህብረተሰቡም ህገወጦችን በመጋለጥ ድጋፉን እንዲያደርግም ድርጅቱ መጠየቁን የዘገበው ኢቢሲ ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE