ኢትዮጵያ አንድ ሀገር ሆና እንድትቀጥል እንፈልጋለን፡፡ – አቶ ሌንጮ ለታ

አቶ ሌንጮ ለታ ይናገራሉ !
• ኢትዮጵያ አንድ ሀገር ሆና እንድትቀጥል እንፈልጋለን፡፡

• ኦነግ ስትራቴጂውን እንዲያሻሽል በውስጥ ሆነን ሃያ አመታት ታግለናል፡፡ ብዙም ግፊት እየፈጠርን ነበር፤ ያ አልተሳካም፡፡

• በደኖና አርባ ጉጉ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ኢህአዴግ ያቀናጀው ትረካ ነው፡፡ ኦነግ የለበትም፡፡

• ኦዴግ የመገንጠል አላማን አይደግፍም፡፡

• እየተካሄደ ያለው ግጭት የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት አይደለም፡፡ የለውጡ ጠላት የሆኑ ኃይሎች ከኋላ ሆነው የሚያቀነባብሩት ይመስለኛል፡፡

• አዲስ አበባን በተመለከተ ይሄ ከተማ የኦሮሞ ዋና ከተማ የፌዴሬሽኑም ዋና ከተማ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ላይ ባንነታረክ ይሻላል፤ ዋጋ የለውም፡፡

ምንጭ ፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE