የተማሪዎችን ሕይወት የቀጠፈው በጠገዴ ወረዳ ቦንብ ተቀብሮ የቆየ አለመሆኑ ታወቀ

የአማራ ክልል የሰላም ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ እንደተናሩት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ ቡሬ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካባቢ ፈንድቶ 2 ተማሪዎችን የገደለውና ሌሎች ስድስት ተማሪዎችን ያቆሰለው ቦንብ እንዲሁ ተቀብሮ የቆዬ አይደለም፡፡

እንደ ጀኔራል አሳምነው ቦንቡ ሆን ተብሎ ለጥፋት የተዘጋጄና ሆን ተብሎ የገባ ነበር፤ የት አካባቢ ጥፋት ለማድረስ ታቅዶ እንደነበር ግን እስካሁን አልተረጋገጠም፡፡

አብመድ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ከዚህ ቀደም ‹‹በመሬት ውስጥ ተቀብሮ ከቆየ ረጅም ዓመታት ያስቆጠረ ኤፍ 1 ቦንብ ፈንድቶ ነው ጉዳት የደረሰው›› ማለቱን ዘግቦ እንደነበር አስታውሷል፡፡ (ኢ.ፕ.ድ)


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE