በሌባ ፖሊስ ተይዞ በሌባ ዐቃቢ ሕግ ተከሶ በሌባ ዳኛ በሚፈረድበት ሃገር እንዴት መንግስት አለ ብለን እናስብ ?

በሌባ ፖሊስ ተይዞ በሌባ ዐቃቢ ሕግ ተከሶ በሌባ ዳኛ በሚፈረድበት ሃገር እንዴት መንግስት አለ ብለን እናስብ ?  አንደኛ ሌቦች ዳኞች፣ ሁለተኛ ሌቦች ዐቃቢ ህጎች፣ ሶስተኛ ሌባ ፖሊስ ሲሆን አራተኛው ሌባ ኦዲተሮች ናቸው ! እንዲሁም የሃይማኖት ሰዎችም ሌቦች ናቸው። ወንጀልን ለመከላከል እና የሌብነት ስራዎችን ለመከላከል የተቀመጠው ኃይል ዋና የወንጀል ፈፃሚ መሆኑ ሀገርና ህዝብን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ ነው።

“በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የተስፋፋውን የሌብነት ወንጀል ለመከላከል የኦዲት ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ የሌብነት ወንጆችን ለመከላከል የኦዲት ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በመንግስት መዋቀር እና የውስጥ አመራር ላይ የሚታዩ የሌብነት ስራዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተለይም በፍርድ ቤት እና ዳኝነት ዙሪያ ያለው የሌብነት ወንጀል ትልቅ ለውጥ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል።

ወንጀልን ለመከላከል እና የሌብነት ስራዎችን ለመከላከል የተቀመጠው ኃይል ዋና የወንጀል ፈፃሚ መሆኑ ሀገርና ህዝብን በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የሃይማኖት ተቋማት የሌብነት ወንጀል እየተስፋፋባቸው ከመጡ ተቋማት መካከል ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከዚህ በኋላ የህግ ማዕቀፍ ተበጅቶ እያንዳንዱ የህዝብ ሃብት በትክክል መዋሉን ለማረገጋገጥ የሚያስችል የኦዲት ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በሁሉም ተቋማት ውስጥ የሚስተዋሉ መሰል የሌብነት ወንጀሎች በማጋለጥ እና ኃላፊነትን በንፁህነት በመወጣት ኢትዮጵያን መድረስ ከሚገባት የልእልና ደረጃ ላይ ማድረስ አንደሚገባም ተናግረዋል።