ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና የተደራዳሪነት አቅሟ ቀነሰ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና የተደራዳሪነት አቅሟ መቀነሱን የፕላን ሚንስትር ፍጹም አሠፋ ለሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት መናገራቸውን ሪፖርተር አስነብቧል።

የአገሪቱ የድርድር አቅም የቀነሰው፣ ከታሪፍ ነጻ ወይም የታሪፍ ቅናሽ የምታደርጋቸውን ሸቀጦችና አገልግሎቶች በቀነ ገደቡ ለአሕጉራዊው ጽሕፈት ቤት ባለማሳወቋ ነው። ነጻ ንግድ ቀጠናው ከዓመት በፊት ከታወጀ ወዲህ፣ 34 አገራት ከታሪፍ ነጻ ወይም የታሪፍ ቅናሽ የሚያደርጓቸውን ሸቀጦችና አገልግሎቶችን አሳውቀዋል።

በሐምሌ በአፍሪካ የሚንስትሮች ስብሰባ በርካታ አገራት ድርድር ይጀምራሉ።