እየተተራመሰ ያለው የአማራ ክልል መንግስት #ግርማካሳ

ኦህዴዶች አራት ኪሎ የገቡት በብአዴኖች ትከሻ ላይ ነበር፡፡ የፈለጉትን ካገኙ በሗላ ግን ብአዴኖችን መቀለጃ ነው ያደረጏቸው፡፡ መሳያቂያ፡፡ አንድ ጆክ ነበር ድሮ፡፡ “አበላል እንደ ደርግ አባል፣ አለባበስ እንደ ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ፣ የአገዳደል ስልቱ እንደ ሊቀመንበር መንግስቱ” የሚል፡፡ አሁን ደግሞ ክሽፈትና ጭንገፋ እንደ አማራ ብልፅግና የሚል ጨምሬበታለሁ፡፡
የአብይ አህመድ ኦህዴድ መንግስት አራት ኪሎን ከተቆጣጠረ አራት አመት ብቻ ቢሆነውም በአማራ ክልል አምስት ጊዜ የአስተዳዳሪ ለውጥ እንዲኖር አስደርጓል፡፡
ለውጥ የተባለው አንዳንዶች ተጭንግፏል/ተቀልብሷል የሚሉት፣ ሌሎች ደጎ መጀመሪያውን የማስመሰል እንጂ ለውጥ አልነበሩ የሚሉት፣ ለውጥ የተባለው ሲመጣ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ነበር የአማራ ክልል ርእስ መስተዳደር፡፡ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለሕዝብ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት በአብይ አህመድና ደምቀ መኮንን ሴራ እንዲለቅ ተደረገ፡፡  ምክትሉ አቶ ላቀ አያሌው በምክትል ርእስ መስተዳድርነት ማእረግ ርእሰ መስተዳደር ሆኖ መስራት ጀመረ:: አንድ በሉ::
አቶ ላቀው አያሌው ለወራት ካስተዳደረ በሗላ፣ እርሱ በሃላፊነቱ ሊቀጥል ሲችል፣ ከጀነራል አሳምነው ጋር ባለው ቅርርብና በክልሉም የአማራ ልዩ ኃይል እንዲጠናከር በማድረጉ እንዲቀጥል አልተፈለገም፡፡ በአዴፓ የባህር ዳሩ ጉባዬ ዶር አምባቸው ትልቁን ድምጽ ያገኘ የነበረ ቢሆንም፣ በደመቀ መኮንን ምትክ የአዴፓ ሊቀመንበርና ምክርትል ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ሲገባው፣ በአሻጥር ደመቀ መኮንን እንዲቀጥል ተደረገ፡፡ ዶር አምባቸውን  ወደ ጎን መግፋት ስላልቻሉ፣  የአማራ ክልል  ር እስ መስተዳደር እንዲሆን ተደርገ፡፡ አቶ ላቀው በዶር አምባቸው ተተካ:: ሁለት በሉ፡፡
ዶር አምባቸው መኮንን ፣ ከአቶ ዪሐንስ ቧያሌው ጋር በመሆን፣ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች በመዞር ፣  የሕዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለማስመለስ ቁርጠኝነት እንድላቸው በመግለስ   በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃትን ፈጠረ፡፡ ቀደም ሲል በባህር ዳር መስተዳደር የተረሱ እንደ ምንጃር ያሉ አካባቢዎች ሳይቀር ነበር እነ ዶር አምባቸው የጎበኙት፡፡የዶር አምባቸው መኮንን ተቀባይነት፣ የነ ጀነራል አሳምነው ሕዝባዊነት በአራት ኪሎ አልተወደደም፡፡  ዶር አምባቸውን በቀላሉ  መቀየር እነ አብይ አህመድ አልቻሉም፡፡ ዶር አምባቸው መኮንን እንዲገደል ተደረገ፡፡  የአብይ እሀመድ ግራ እጅ 9ቀኝ እጂ ሺመልስ አብዲሳ ነው)  ተመስገን ጥሩነህ  ቦታዉን ያዘ፡፡ ሶስት በሉ::
ተመስገን ጥሩነህ ክልሉ በኦህዴድ ስር እንዲወድቅ የሚሰራውን የአፈና መዋቅር በአማራ ክልል ከዘረጋ በኋላ፣ ለና የሚታዘዝ ነው በሚል፣ አገኘው ተሻገር እንዲተካ ተደረገ፡፡ አራት በሉ::
አገኘሁ ተሻገር ወያኔ ወረራ ስትፈፅም ስህተቶች ቢሰራም፣  በአንፃራዊነት ትላልቅ መልካም ውሳኔዎች አሳለፈ፡፡ እነ ጀነራል ተፈራን አመጣ፡፡  ህዝብን አንቀሳቀሰ፡፡  ይህ አልተወደደለትም፡፡ “እኛው ስር ሆኖ እንቆጣጠረዋለን” ተብሎ ወደ ፌዴራል እንዲሄድ ተደረገ፡፡ በምትኩ ይልቃል ከፍያለ የተባለ፣ ማንነቱ የማይታወቅ፣ እነ አብይ አህመድና ተመስገን ጥሩነህ ኝ አስቅድመው ያዘጋጁት የኦህዴድ ቀጥተኛ ተላላኪ  ቦታዉን እንዲይዝ ተደረገ፡፡ ይህ ሰው እንሆ አሁን የኦህዴድ በትር ሆኖ ፣ ጀነራል ተፈራ ማሞ እንዲነሱ ካድረገ በኋላ፣ የኦህዴዶች መመሪያ በቀጥታ በመቀበል ፋኖን ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጇል፡፡ አምስት በሉ:፡፡
እነ አብይ አህመድ የክልሉን ህዝብ አንገት ለማስደፋት የሚያደርጉት የተሳካላቸው አይመስልም:: በነርሱ የማይጋለብ መሪ ባህር ዳር ካለ ይቀይሩታል ወይም ያስገድሉታል:: የነርሱን ሰው ካስቀመጡ በሗላ ደግሞ እንዳሰቡት ካልሆነላቻው እንደ ሸሚዝ አውልቀው ይቀይሩታል::
የአሁኑ መሪ ይልቃል ከፍ ያለ ከነርሱ መመሪያ ተቀብሎ በፋኖ ላይ ዘመቻ መጀመሩ ሰውዬው  ዶክተር የሚል ማእረግ ያለው ቢሆንም፣ የት ነው የተማረው እስኪያሰኝ ድረስ  እውቀትና ማስተውል የጎደል ሆነ ነው የተገኘው፡፡ ትልቅ ስህተት እየፈጸመ ነው፡፡ ላያዋጣው ከህዝብ ጋር መጣላት ጀምሯል፡፡ ያንንም በማድርጉ ከነ በረከት ስምኦን፣ ከነ ታደሰ ጥንቅሹ  በበለጠ እየተጠላ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ትንሽ የማፈግፈግና የመፍራት ነገር እየታየበት እንደሆነ እየተሰማ ነው፡ ያንንን ተከትሎ አብይ አህመድ ሊያነሳውም ይችላልም ተብሎ ይጠበቃል::
የአማራ ክልል መንግስት ለህዝብ የወገነ መስተዳደር ካላገኘ፣ የኦህዴዶችን ጣልቃ ገብነት ካላስቆመ፣ ተጠሪነቱን ለአራት ኪሎ መሆኑ ቀርቶ ለህዝብ ካልሆነ፣ ትልቅ ችግር ነው የሚፈጠረው፡፡ በመሆኑም ለክልሉ ሰላም ሲባል እንጥፍጣፊ የህዝብ ፍቅር ካላቸው የአማራ ብልፅግና ነን ባዮች ከሌሎች ሃይሎች ጋር በመተባበርና በመነጋገር የተሻለ አቅጣጫ ማስቀመጥ መጀመር አለባቸው፡፡
ከዚህ በታች ላለፉት አራት አመት የተፈራረቁ ስድስት አመራሮች ናቸው፡፡  ከነዚህ መካከል እንዱ ነፍሱን ይማረውና ዶር አምባቸው መኮንን ነበር፡፡