የደራ ጥያቄን ተከትሎ ቅምብቢት፣ አቢቹ፣ አዳማ ….መቀጠላቸው አይቀርም #ግርማካሳ

ከአንድ አመት በፊት በደራ ጉዳይ ሰፋ ያሉ ጦማሮች ለቅቄ ነበር። በተለይም በኦሮሞ ክልል የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰባት ላይ የሚደርሰው በደል፣ አፓርታይዳዊ ተጽኖና አድልዎ እንደማያዋጣና አንዱ የበላይ ሌላው የበታች ሳይሆኑ ሁሉም ዜጎች እኩል የሚታዩበት ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አጠንክሬ ለረጅም ጊዜ ተከራክሪያለሁ።

በተለይም ኦሮሞና አማራ የተደባለቀ፣ ለዘመናት አብሮ የኖረ በመሆኑ፣ ኦሮሞንና አማራን በክልል መለየት መዘዙ በጣም የከፋ እንደመሆነ በማሳሰብ ፣ በተለይም ኦሮሞዉም አማራዉም እኩል የሚታዩበት፣ ኦሮምኛና አማርኛ የስራ ቋንቋ የተደረጉበት ሸዋ የሚባለ የፌዴራል መስተዳደር እንዲኖር ክፊት አድርጊያለሁ።

የአማራዉና የኦሮሞዉን መተሳሰር ዶ/ር አብይ “አማራና ኦሮሞው ሰርገኛ ጤፍ ናቸው” በማለት፣ አቶ ገዱ ደግሞ “አማራና ኦሮሞ ሰምና ፈትል ናቸው” በማለት ነበር ለማሳየት የሞከሩት። አሁንም አቶ ገዱን በመጥቀስ “ኢትዮጵያ ውስጥ በደንብ ቢጠና የአማራና የኦሮሞን ያህል የተቀላቀለ ህዝብ የለም” ።

ከአመት በፊት በጦመርኩት፡

“በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ደራ ውስጥ የተወለደ አማራ ገበሬ ክልሉ ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ ፍርድ ቤት ለመሔድ የአማርኛ ማመልከቻውን፣ ደረሰኝ ወዘተ በኦሮምኛ አስተርጉሞ መቅረብ አለበት፡፡ በዚህ መልኩ ገበሬው ለብጣሽ ሪሲት ሳይቀር መቶ ብር ወይም ከዚያ በላይ አውጥቶ ያስተረጉማል፡፡ ብዙ ኢንተርፕራይዞችም የአማርኛ ደብዳቤን በማስርጎም ሥራ የደሃ ገበሬዎችን ሀብት ይዘርፋሉ፡፡ በዚህም ምክንያት 20 ወይም 30 ገጽ ያለው አቤቱታ ለማስተርጎም ብዙ ሺህ ብሮች ስለሚያስፈልግ ከፍትኅ ሥርዓቱ እንዲገለሉ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ በመሠረቱ እንኳንስ ትንሽ የማይባሉ ዜጎች ያሉበት አካባቢ ሆኖ አንድ ሰውም ቢሆን በራሱ ቋንቋ ፍትኅ ማግኘት የሚያስችል ሥርዓት መኖር መቻል ነበረበት፡፡ ከዚህም በከፋ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ትምህርት የመማር መብት የሌላቸው ዜጎች ሚሊዮኖች ናቸው” በሚል በክፍፍሉ የተጎዱ ወገኖች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ነበር የገለጽኩት።

ስለ ደራም ፣ “በኦሮሞ ክልል የተረሳ፣ አማርኛ ተናጋሪዎች በብዛት ያሉበት ወረዳ ነው። የደራ ወረዳ። ወረዳው መጀመሪያ ደረጃ ለምን ወደ ኦሮሞ ክልል እንደተቀላቀለ ግልጽ አይደለም። በሁለተኛ ደረጃ በወረዳው አንድ በኦህዴድ የተሰራ ትምህርት ቤት፣ ብጣሽ መንገድ..አለመኖሩ በአገሪቷ ያለውን ኢፍትሃአዊነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ” በማለት የደራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን አጋልጫለሁ።

በደራ አማርኛ ተናጋሪው ከ75% በላይ ነው። በቅምቢብት ከ 60%፣ በአብቹ ደግሞ ከ 50% በላይ።

እነዚህ ወረዳዎች አማራ ክልል ጋር የገጠሙ ሲሆን ወደ ኦሮሞ ክልል ግን እንዲጠቃለሉ ተደርጓል።ምክንያቱን ቢጠየቅ የሚሰጠው መልስ ግጽና ቀላል ነው። የአማራ ማህበረሰብ ሕወሃትና ኦነግ አገሪታኡን ሲሸነሽኑ “ተሸናፊ” ስለነበረ ብዙ አማርዎች ወይንም አማርኛ ተናጋሪዎች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ወይ ወደ ትግራይ አሊያም ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲጠቃለሉ ተደርጓል።

ደራ፣ አካባቢዉ ወደ 13 ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን በጎጃም የአባይ ወንዝ፣በወሎ የወለቃ ወንዝ፣በመረሀቤቴ የወንጪት ወንዝ እና ወደ አዲስ አበባ የጀማ ወንዝ ያዋስኑታል። አማርኛው ተናጋሪው ከከ80% በላይ ሆኖ ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲጠቃለል ተደረጎ ለሃያ ሰባት አመታት ኦሮምኛ ብቻ የስራ ቋንቋ በተደረገበት፣ አፓርታይዳዊ ዘረኛ የኦሮሞ ክልል እስጥ ሁለተኛ ዜጋ ተደረገው ሲኖሩ ነበር።

የደራ ህዝብ በአሁኑ ወቅት ድምጹን እያሰማ ነው። እክሉእንት፣ ፍትህ እያለ ነው። በአገራችን ሁለተኛ ዜጋ ተደረጎ መቂጠር ይብቃ እያለ ነው።፡ኦሮምኛ ባለመቻላችን ጭቆና አይፈጸምበን እያለ ነው።

አሁንም መፍትሄው የአማራ የኦሮሞ ክልል ሳይባላ ይሆእ በታሪካ አብሮ የኖረን፣ የተዋለደን ማህበረሰብ ሸዋ በሚል መስተዳደር ውስጥ፡ማቀፉ ብቻ ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US