የኦነግ ሸኔ ጦር በርካታ የኦሮሚያ ወረዳዎችን በተቆጣጠረበት ወቅት ላይ ሆነው በሸኔ የተያዘ አንድም ወረዳ የለም መባሉ እያነጋገረ ነው።

  • ባለስልጣኑ እውነትን ለመደበቅ የሄዱበት መንገድ ያሳፍራል።

አንድ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ባለስልጣን በኦሮሚያ ክልል በፊትም ሆነ በአሁን ወቅት በሸኔ ቁጥጥር ሥር የዋለ ወረዳም ሆነ ቀበሌ የለም ሲል የክልሉ የጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡ መንግሥት በአሸባሪ ቡድኑ ላይ የተሳካ ዘመቻ እያካሄደ ነው ሲል መናገራቸው የባለስልጣናት ውሸት ልኩን እያጣ መሆኑ ግልፅ አድርጎታል።

የኦነግ ሸኔ ጦር ሙሉ ወለጋን ከፊል ሸዋን እና ከፍል ጉጂን እንዲሁም ባሌሎች የኦሮሚያ አከባቢዎች በርካታ ወረዳዎችን ተቆጣጥሮ እያለ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ላይ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና የጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ አሸባሪው የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል የተቆጣጠራቸው ቦታዎች እንዳሉ ቢነገርም ቡድኑ ከበፊትም ጀምሮ እስካሁን ድረስ የተቆጣጠረው ወረዳ፣ ቀበሌ አሊያም ምንም መንደር የለም፡፡ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በአሸባሪው የሸኔ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለው ዘመቻም የተሳካ ሆኗል፡፡ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

No description available.በኦሮሚያ ክልል የኦነግ ሸኔ ጦር በወለጋ ዞኖች፤ በሸዋ፣ በባሌ ተራሮች፣ በሃረርጌና በጉጂ አከባቢዎች በርካታ የማሰልጠኛ ካምፖች አሉጥ በርካታ ሰራዊትም አሰልጥኖ በማሰማራት ከፍተና ጥቃት እየፈጸመ በሚገኝበት ወቅት ላይ የጸጥታ ኃላፊው እውነትን ለመደበቅ የሄዱበት መንገድ እጅግ የሚያሳፍርና የሕዝብን ሰላምና ደሕንነት ለጥቃት የሚያጋልጥ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ ።

በርካቶች እየተገደሉ እና እየተፈናቅሉ ፣ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከሕዝቡ ግብር እየሰበሰቡ፣ መንገድ ላይ ቆመው ቀረጥ እያስከፈሉ፣ ማዳበሪያ እያከፋፈሉና ነዳጅ እየነገዱ፣ የወረዳ ቀበሌ ጽ/ቤቶችን ተቆጣጥረው የራሳቸውን መንግስት መስርተው እየመሩ ባሉበት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ሁኔታ በመንግስት ሚዲያዎች ሕዝብን ለማታለልና ለማዘናጋት የሚፈልጉት የመንግስት ባለስልጣናት የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ አደገኛ ነው። የመንግስት ባለስልጣናት ውሸታቸውን ሊያቆሙ ይገባል።