የአፋር ክልል አስተዳደር የሕዝቡን ኑሮ ከመለወጥ ይልቅ የክልሉን ሕዝብ መከራውን እያሳየው መሆኑ ተገለፀ

እዮብ ዘለቀ

የአፋር ህዝብ በማንነቱ በ ኢትዮጵያዊነቱ እና በባንዲራው የማይደራደር ኩር ኢትዮጵያዊ ነው ፤ ሆኖም ግን ክልሉን የሚያስተዳድረው አብዴፓ ላለፋት በርካታ አመታት የአፋር ህዝብን ወደ ተሻለ የእድገት ጎዳና ከመምራት ይልቅ በጎሳና እና በቤተሰብ በመቧደን ፤ የክልሉን ሕዝብ መከራውን እያሳየው መሆኑን ማንም የሚመስክረው ሀቅ ነው ።

የአፋር ህዝብ ለ 20 አመት ያህል ያለማንም ተቀናቃኝነት በኢስማኤል አሊ ሴሮ ተመርቷል ፤ በእነዚህ ዘመናት የአፋር ህዝብ ላይ የደረሰው ስቃይ ተወርቶ አያልቅም ፤ እስማኤል አሊ ሴሮን ተክተው በ2007 ዓ.ም ወደ ስልጣን የመጣው የሀጂ ስዩም አወል አስተዳርደም ከቀድሞው በከፋ መልኩ ህዝቡን ለድህትና ለመከራ ዳርጔል ላለፋት 3 አመታት ክልሉን በተገቢው መንገድ መምራትም ተስኖታል ፤ በተለያዩ ጊዜያት በክልሉ መግንስት ላይ የሚደርሱ ተቃውሞውችን በሀይል ለማፈን ሲሞክሩ በርካቶች ላይ ጉዳት ደርሷል ፤ ለስደት የተዳረገውም ወጣትም ስፍር ቁጥር የለውም።

ይህም በፓርቲው ውስጥ ከፍተኛ ውጥረትም ፈጥሯል ፤ የመከፋፈል አዝማሚያዋችም ታይተዋል ፤ ሆኖም ግን አብዛኛው የአፋር ህዝብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተቃውሞውን ማሰማቱን ለአፍታም አልቋረጠም ፤ በዚህ ረገድ የአፋር ወጣቶች /ዱኩሂና /ከባድ መስዋትነት ከፍለዋል ።

በአሁኑ ሰአት 7 ተኛው የአብዲፓ መደበኛ ጉባኤ በአፋር ክልል ሰመራ እየተካሄደ ነው ፤ ጉባኤው አሮጌዋቹን አመራር አራግፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጣውን ለውጥ የሚያሳካ በወጣት የተገነባ አዲስ አመራር ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል ፤ ይህ ከሆነ መጨው ጊዜ ለአፋር ወጣቶች እንዲሁም ለመላው የአፋር ህዝብ ብሩህ ይሆናል ።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE