‹‹ለውጡ ስር እንዲሰድና ህዝቡ የዴሞክራሲ ባለቤት እንዲሆን ልታግዙን ይገባል፡፡›› ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው

‹‹ብዙ ስልጣን ማን ያዘ? ማን ምን ሆነ? የሚለው ጥያቄ ለዚህ ትግል አይመጥንም፡፡የለውጡ እንቅስቃሴ ከስልጣን ያለፈ ዓላማ እና ግብ ያነገበ ነው፡፡››

‹‹ለውጡ ስር እንዲሰድና ህዝቡ የዴሞክራሲ ባለቤት እንዲሆን ልታግዙን ይገባል፡፡›› ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው

(አብመድ) ለአማራ ህዝብ ህልውና ብሎም ለኢትዮጵያ ልዕልና በአንድነት እንስራ! በሚል መሪ ሃሳብ በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራ ልዑክ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ትናንት በዲሲ በነበራቸው የምክክር መድረክ ከተወያዮች ለተነሳላቸው ጥያቄ የልዑካን ቡድኑ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በውይይቱም በጣና ሃይቅ ላይ ስለተጋረጠው አደጋ፣ የወሰን ጉዳይ፣ ጫት፣ ሰላም እና ሃገራዊ አንድነትን የሚመለከቱ ጥያቄዎች ተነስተው ነበር፡፡

አሁን ያለው የለውጡ እንቅስቃሴ ከስልጣን ያለፈ ዓላማ እና ግብ ያነገበ ነው፡፡ ለውጡ ተቋማዊ እና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን የሁላችንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ብዙ ስልጣን ማን ያዘ? ማን ምን ሆነ? የሚለው ጥያቄ ለዚህ ትግል አይመጥንም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ መስዋትነት የተከፈለው ኢትዮጵያ ለዜጎቿ የተመቸች ሃገር እንድትሆን ነውና የተጀመረው ለውጥ ስር እንዲሰድ ህዝቡ የዴሞክራሲ ባለቤት እንዲሆን ልንተጋገዝ ይገባል ብለዋል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE