ሶስት ኩንታል ዶላር አፋር ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ሶስት ኩንታል ዶላር አፋር ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ብዙ ሰዎች “በአፋር ክልል አዳአር_ወረዳ ደርሳጊታ ቀበሌ ላይ ሶስት_ኩንታል ዶላር የጫነች ቪትዝ መኪና በቁጥጥር ስር ዋለ!” የሚል መረጃ በፌስቡክ ስመለከት ገዳዩን ለማጣራት ወደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ባልደረባ ስልክ ደወልኩ፡፡

በእርግጥ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ “ሶስት ኩንታል ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ” የሚል መረጃ ማመን በጣም ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን ስልክ ደውዬ የመረጃውን ትክክለኝነት ለማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ ከታች በምስሉ የሚታዩት መኪኖች የቆሙት በአፋር_ሰመራ ፖሊስ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡

ዶላሩ በቁጥጥር ስር የዋለው በቪክሷ መኪና ተጭኖ ሲዘዋወር ነው፡፡ ጥቁሯ መኪና ደግሞ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ዶላር ጭና ስትንቀሳቀስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለች እንደሆነ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE