ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ 12 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ 12 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

(ኢ.ፕ.ድ) ፤ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው፣ ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው፣ የአለም ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለቤት አቶ አለም ፍጹም እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ ከ10 በላይ ተጠርጣሪዎች ለ2ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው እለት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ የሰራውን የተናጠል ምርመራ ለችሎቱ ያቀርባል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ነው።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE