በአምቦ፣ በጅማ፣ በግምቢ እንዲሁም የተለያዩ ቦታዎች ተቃዉሞ እንቅስቃሴ መኖሩ ተሰማ

በኦሮሚያ ክልልና በቤንሻንጉል ጉሙዝ አዋሳኝ ድንበሮች አካባቢ የተከሰተዉን ግድያና መፈናቀል በመቃወም ዛሬ በአምቦ፣ በጅማ፣ በግምቢ እንዲሁም የተለያዩ ቦታዎች ተቃዉሞ እንቅስቃሴ መኖሩን የዓይን እማኞች ለDW ተናግረዋል።

በተቃዉሞዉም መምህራን፣ ተማሪዎች እንዲሁም የፀጥታ አስከባሪ አባላት መሳተፋቸዉንም ገልፀዋል። ካነሷቸው ጥያቄዎችም በማኅበረሰቡና በፀጥታ አካላት ላይ የሚደርሰዉ ግድያ ይቁም፣ ጥፋተኞች ለፍትሕ ይቅረቡ፣ የመሬት ነጠቃና ገበሬዎች ማፈናቀል ይቁም የሚሉት ይገኙበታል። ተቃዉሞዉ የሚካሄደው እስካሁን በሰላም መሆኑንም እማኙ አመልክተዋል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀጥታ ምክር ቤት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ድንበሮች ላይ የፌዴራል የፀጥታ አስከባሪ ኃይላት እንዲሰማሩ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት መግለጫ ያመለክታል። የፀጥታ አካላቱ መሰማራት ያለዉን ችግር ለመቆጣጠርና ሰላምን ወደ ቦታው ለመመለስ ምን ያህል ይረዳል ብለው ያስባሉ? አስተያየትዎን ያጋሩን። ይህን ሊንክ በመጠቀም የድምፅ እና የጽሑፍ አስተያየትም መላክ ይቻላል። — http://bit.ly/1QuJh1n


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE