የማፍያ ቡድኑን ለማጥፋት  ተላላኪዎቹን ማስወገድ!!

ስዩም ተሾመ … የማፍያ ቡድኑን ለማጥፋት  ተላላኪዎቹን ማስወገድ!!

እነዚህ ሁለት አባቶች ልጃቸው ሞት ምክንያት ልባቸው በሀዘን ተሰብሯል፡፡ በእርግጥ መኖሪያቸው ወሎ እና ወለጋ ነው!! የሚናገሩት ቋንቋ አማርኛ እና ኦሮምኛ ነው፡፡ አንዱ አባት እጆቹን አጣጥፎ በሀዘን ኩርምት ብሎ ተቀምጧል! ሌላኛው አባት እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል፡፡ ሁለቱም በልጃቸው ሞት የደረሰባቸው ሀዘንና መከራ፣ ስቃይና ሰቆቃው አንድና ተመሣሣይ ነው፡፡ ይሄ ብቻ አይደለም! የሁለቱም ልጆች የተገደሉት #በቤኒሻንጉል_ጉሙዝ መዘዝ ነው፡፡ በክልሉ ግጭትና ብጥብጥ እንዲነሳ የሚፈልገው እና ያደረገው በጌታቸው አሰፋ የሚመራው #የማፊያ_ቡድን ነው!!! ሌሎች አባቶችን ከተመሣሣይ ስቃይና ሰቆቃ መታደግ የምንችለው ይህን የማፍያ ቡድን ጨርሶ በማስወገድ ነው፡፡ ይህ የማፍያ ቡድን የሚወገደው ደግሞ የእሱን የትርምስ አጀንዳ የሚያስፈፅሙ ተላላኪዎች ጨርሶ ሲጠፉ ነው፡፡ የእነሱን የትርምስ አጀንዳ ለማስፈፀም የሚልከሰከሱ ሰዎች ከየትም የመጡ ሳይሆን ከእኛው መካከል የወጡ ናቸው፡፡ ከእኛው ጋር እየኖሩ፣ ከእነሱ ጋር በጥቅም የተሳሰሩ እና እኛን እርስ-በእርስ ለማባላት ዘወትር የሚያሰሩና የሚሰሩ ሰዎች ከሌሉ በጌታቸው አሰፋ የሚመራው ማፍያ ቡድን ምንም ነው፡፡ ስለዚህ የማፍያ ቡድኑን ለማጥፋት ተላላኪዎቹን ማስወገድ የግድ ነው!!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE