አሜሪካ ከኤርትራ ጋር የነበራትን ያሻከረ ግንኙነት ለማሻሻል እንደምትሰራ አስታወቀች

አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታጠናክር ገለጸች

አሜሪካ ከኤርትራ ጋር የነበራትን ያሻከረ ግንኙነት ለማሻሻል እንደምትሰራ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ክፍል ረዳት ሚኒስትር ቲቦር ናጂ እንደገለጹት አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አይነት የተሻለ ግንኙነት ከኤርትራም ጋር ትመሰርታለች ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራ ሰላም ማውረዳቸውን ተከትሎ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ እ.አ.አ ከ2009 ጀምሮ ጥሎት የቆየውን ማዕቀብ እንዲነሳ አሜሪካ ድጋፍ ማድረጓ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፤ ፍራንስ 24


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE