ስብሰባ ጨርሼ ስመለስ፣ ለጓደኞቻቸው ደውለው አዲስ አበባ አሳፈኑኝ ! – መስከረም አበራ

ጋዜጠኛ መስከረም አበራ እውነቱን አጋለጠች
ከማእከላዊ የወጣ ድብቅ መረጃ
ስብሰባ ጨርሼ ስመለስ፣ ለጓደኞቻቸው ደውለው አዲስ አበባ አሳፈኑኝ – መስከረም አበራ
“አቶ ግዛቸው ሙሉነህ…ከእኛ በላይ አማራ አይደላችሁም፤ አማራ አማራ እያላችሁ አታላዝኑብኝ ብሎኛል”
የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በአማራ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ጦማሪዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና ፀሐፊዎችን ባለፈው ግንቦት 10/2014 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ለምክክር ጠራን። የምክክሩ አጀንዳ “የአማራ ህዝብ ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ እንዲወጣ፣ ከእኛ ምን ይጠበቃል?” የሚል ነበር።
ብዙ ጓደኞቼን በጥሪው ዙሪያ አማከርኳቸው። አብዛኞቹ ብአዴንን አምነን ወደ ባህርዳር አንሄድም አሉኝ። እኔ ግን ምክክሩ ስለ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ከሆነ ግድ የለም ልሂድ ብዬ ወደ ባህርዳር ሄድኩ። በስብሰባውም ተካፈልኩ። ሰብሳቢው ደግሞ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ነበር። ከሄድኩ አይቀር ብዬ ስለ አሳረኛው አማራ የተሰማኝን ሁሉ ተናገርኩ።
ነገር ግን ሀሳባችንን ከተቀበሉ በሗላ የስብሰባው አጀንዳ ሙሉ በሙሉ ተቀየረ። ዛቻና ማስፈራሪያ ሆነ። ፋኖን መዝለፍ፣ እኛን ማንጓጠጥ ጀመሩ።
እናንተ ከእኛ በላይ አማራ አይደላችሁም፣ አማራ አማራ አትበሉብኝ እያሉ ለማሸማቀቅ ጀመሩ። እኔ በግሌ ዛቻውን ከቁብ አልቆጠርኩትም። እንዴውም የበለጠ ሀሳብ ሰጠሁኝ። በዚህ አስተያየታችን እዚያው በስብሰባ አዳራሽ እያለን እንዳያስሩን ጨነቃቸው።
በሗላ ጨርሸ ስመለስ፣ ለጓደኞቻቸው ደውለው አዲስ አበባ አሳፈኑኝ።
(መስከረም አበራ – ማዕከላዊ ማረሚያ ቤት ሊጠይቃት ለሄደ እንግዳ የተናገረችው)