የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በላይ ጠላት የለውም (አብረሃ ደስታ)

የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በላይ ጠላት የለውም

(አብረሃ ደስታ)

ባሁኑ ሰዓት የትግራይ ህዝብ ከህወሓት በላይ ጠላት የለውም። ሌላ ጠላት እንዳለ በማስመሰል ህዝብ እንዳይረጋጋ የሚያደርጉት የስልጣን ዕድሜያቸው ለማራዘም ነው። ሌላ ጠላት ከመጣ አብረን እንታገለዋለን።

አሁን ያለው ብቸኛ ጠላት ግን ህወሓት ነው። ለትግራይ ህዝብ ሰላም፣ ፍትሕ፣ አንድነትና እኩልነት ሲባል ሁላችን ለትግራይ ህዝብ የምንቆረቆር ሰዎች ፀረ ህወሓት መነሳት ይኖርብናል።

የትግራይ ወጣት ስራ አጥቶ እየተንከራተተ ባለስልጣናት ዊስኪ የሚጠጡበትን ገንዘብ የሚዘርፉበት ስልጣን እንዳያጡ `ጠላት መጣ` እያሉ ያጭበረብራሉ እነሱ ራሳቸው የወጣቱ ዋነኛ ጠላት ሆነው ሳለ።

አሁን ህወሓትን በጋራ እንታገል፤ ሌላ ጠላት ከመጣ ደግሞ አብረን እንዋጋለን። አሁን ለትግራይ ህዝብ ነፃነት ሲባል ህወሓት በትግራይ ህዝብ ትግል ይውረድልን፤ ከሚቀጥለው ምርጫ ማለፍ የለበትም። ህወሓት ከአንድ ዓመት በላይ ዕድሜ ሊኖረው አይገባም። It is so!!!


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE