መንግስት ፋኖ ሰብሳቢ አርበኛ ዘመነ ካሴ አፈሙዝ ማዞሩ እጅግ የከፋ ደም አፋሳሽ መሆኑን አውቆ ከዚህ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲታቀብ እናሳስባለን ::

ከአማራ ወጣቶች ማህበር አዲስ አበባ ሸዋ ቅርንጫፍ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

ከሰሞኑ ፋኖ ላይ እየተደረገ ያለው የጦር ዘመቻ በአማራ ጋዜጠኞች የማህበረሰብ አንቂዎችና ፖለቲከኞች ላይ እንዲሁም ፖለቲካዊ ንቃታቸው ከፍ ባለ አማሮች ላይ ሁሉ እየተፈፀመ ያለው እስራትና አፈና እና ወከባ ኦሮሞ መር የሆነው መንግስት አማራን ከምድረ ገፅ ለማፅፍት የሚያደርገው ወረራ ዋነኛ አካል ሆኖ አግኝተነዋል ይህ አጥፍቶ የመውረር እንቅስቃሴ ርዕዮተ አለማዊ መሰረት ያለው እንደሆነም እናምናለን

ከምንግዜውም በበለጠ በኦሆዴድ ብልፅግና ዘመን አማራ በጅምላ ተገድሎ በጅምላ የሚቀበር ህዝብ ሆኗል ::

እኛ የአማራ ወጣቶች እስከአሁን ለአብሮነት ስንል ታግሰናል::ነገር ግን ጨፍጫፊዋች የአውሬነት ባህሪን እየተላበሱ ይበልጥ ከሰባዊነት እየራቁ መጥተዋል :: መንግስት ከግብረ አበሮቹ ጋር በአማራ ላይ የሚያደርሰውን የዘር ፍጅት ወከባ አፈና እና ማሳደድ ብሎም በፋኖ ላይ የአወጀውን ተደብቆ የማጥቃት የክህደት ውጊያ በአስቸኳይ የማያቆም ከሆነ እራሳችንን ከግድያ የመከላከል ተፈጥሮአዊ መብታችንን ለመጠቀም የምንገደድ መሆኑን እናሳውቃለን:: በአዲስ አበባ አማራ የሆንን ሁሉ እያሳደዱ ማፈንና ማሰርና ማገት በአስቸኳይ የማይቆም ከሆነ እኛ በአፅመ እርስታችን አዲስ አበባ የመኖር የአማራ ወጣቶች ከዚህ በላይ የማንታገስ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን:: በመሆኑም

፩. መንግስት ወደ አማራ ህዝባዊ ሆይል(ፋኖ) ሰብሳቢ አርበኛ ዘመነ ካሴ አፈ ሙዝ ማዞሩ እጅግ የከፋ ደም አፋሳሽ መሆኑን አውቆ ከዚህ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲታቀብ እናሳስባለን ::

፪. መንግስት ጀግኖች ፋኖዋች በሌሉበት ቤታችውን እየበረበረ ጭምር ከፋኖ የነጠቃቸውን መሳሪያዎች እንዲመልስ እንጠይቃለን ::

፫. በተለያዩ የአማራ ከተሞች በተለይም በሞጣ በወልዲያ እና በመራዊ በኑፁሀን ህይወት ላይ እና በንብረት ላይ ላደረሰው ጉዳት መንግስት ተመጣጣኝ ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን::

፬. በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ እና በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ላይ እንዲሁም በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ እና በአንጋፋው ጋዜጠኛ የታሪክ ፃሀፊ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ጨምሮ ከላይ በአማራዊ አስተሳሰባቸው ምክንያት የታሰሩት ሁሉ በአስቸኳይ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ ዶሴው ተቋርጦ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን::

አማራነት ወንጀል አይደለም

ግንቦት 16 ቀን 2014 አ.ም
የአማራ ወጣቶች ማህበር አዲስ አበባ ሽዋ ቅርንጫፍ

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ