በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የፌድራል መንግሥት የጸጥታ አስከባሪዎች እንዲሰማሩ ተወሰነ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የፌድራል መንግሥት የጸጥታ አስከባሪዎች እንዲሰማሩ ወሰነ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልሎች ጥያቄ መሠረት መሆኑን የጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ከውሳኔው የደረሰው ኅዳር 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በአካባቢው በተፈጠረው «የጸጥታ ችግር እና ሰብዓዊ ቀውስ» ላይ ውይይት ካካሔደ በኋላ መሆኑን የጠቅላይ ምኒስትር ፅህፈት ቤት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በመግለጫው መሠረት የአገሪቱ ብሔራዊ ጦር እና የፌድራል ፖሊስ በአካባቢው እንዲሰፍር የተወሰነው “የአካባቢውን ሰላም የማስከበር፣ የዜጎችን ህይወት የመታደግ እና በአካባቢው የህግ የበላይነትን በማስከበር አስተማማኝ ሰላም እና ጸጥታን የማስፈን ጉዳይ ከሁለቱ ክልሎች አቅም በላይ” ሆኖ ስለተገኘ እንደሆነ አትቷል።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE