በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋት የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋት የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው እንዳሰፈሩት፥ ፖሊስን ጨምሮ በአካባቢው የበርካታ ነዋሪዎችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ በማጥፋትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ 66 ሰዎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አቶ አዲሱ አያይዘውም የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።ዘገባው ኤፍ.ቢ.ሲ ነው፡፡


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE