ህወሃት የአክሱም ሙስሊሞች ለመደበቅ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም ።

ህወሃት የአክሱም ሙስሊሞች ለመደበቅ ያደረገችው ጥረት አልተሳካም ።

የአክሱም ሙስሊሞች ዛሬ ጁማም እንደወትሮው በተለመደው ሰዓትና ቦታ በሰላም ሶላታቸውን ሰግደዋል ። ምንም እንኳ ለዛሬ የሚደረገው የጁማ ሶላት ከማርያም ጽዮን በዓል ጋር በሚል ሰበብ እንደወትሮው ከህዝብ እይታ ልትሰውራቸው አስባ የነበረ ቢሆንም በአሏህ (ሱወ) ፈቃድና የአክሱምና ሌሎች ሙስሊሞች ባደረጉት ትግል የጁማአ ሶላታቸውን በተለመደው ሰዓትና ቦታ በሰላም መስገድ ችለዋል ።

በአገር ውስጥም በውጭም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት ትግል ሊደነቅና ሊመሰገን ይገባል ። ይህ ጥንካሬ የአክሱም ሙስሊሞች እንደማንኛውም ሰው መስጅድና መቀበሪያ እስኪያገኙ ድረስ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE