ስልጣናቸዉ ወይም የኢኮኖሚ ጥቅማቸዉ የተነካ ለዉጡን ወደ ኋላ ለመመለስ በተለያዩ ቦታዎች ዘግናኝ ወንጀሎች እየፈፀሙ ነዉ

ከስብሰባዉ በኋላ የወጣ መግለጫ «ስልጣናቸዉ ወይም የኢኮኖሚ ጥቅማቸዉ የተነካ ለዉጡን ወደ ኋላ ለመመለስ በተለያዩ ቦታዎች ዘግናኝ ወንጀሎች ኢየፈፀሙ ነዉ» ይላል።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚታየውን የፖለቲካ አለመረጋጋትና የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ትላንት ስብሰባውን አካሂዷል። ከስብሰባዉ በኋላ የወጣ መግለጫ «ስልጣናቸዉ ወይም የኢኮኖሚ ጥቅማቸዉ የተነካ ለዉጡን ወደ ኋላ ለመመለስ በተለያዩ ቦታዎች ዘግናኝ ወንጀሎች ኢየፈፀሙ ነዉ» ይላል።

በምዕራብ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የወሰን አካባቢዎች፣ እንዲሁም ምሥራቅ ኦሮሚያን ከሶማሌ ክልል ጋር በሚያዋስኑ ቦታዎች ላይ «የታጠቁ  አካላት» በንፁሃን የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ርምጃ ኢየወሰዱ ነዉ ሲባል በተደጋጋሚ ይሰማል። እነዝህን የታጠቁ ኃይሎች ክልሎች የሚያውቁዋቸው ከሆነ ለምን ርምጃ አይወስዱም? ከክልሎቹ ኢዉቅና ዉጭ ከሆኑ ደግሞ ክልሎቹ  ከፌዴራል ኃይሎች ጋር በመሆን ለምን ርምጃ አይወስዱም የሚሉ ጥያቄዎች ከማህበረሰቡ ይቀርባሉ። እነዚህን ጥያቄዎች ለኦሮምያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፋ አቅርቤላቸዉ ነበር። እነዝህ አካላት ግጭቶችን ለማስቀጠል ለመጨረሻ ግዜ ኢየተፍጨረጨረ እንደምገኝ አቶ ዴሬሳ ገልፀዉ መንግስታቸዉ ከፌዴራልና ከለሎች ክልሎች ጋር በመሆን ኢየሰራ እንደምገኝ አክሎበታል።

የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ «ይህ የመቃብር አፋፍ ላይ የደረሰው ህልማቸው ወደ መቃብር ይወርዳል እንጂ መቼም ቢሆን የኦሮሚያ ክልልን የብጥብጥ እና የጦርነት አውድማ አያደርጋትም» ሲል በመግለጫው አመልክቷል። «ባርነትን እና የሰብዓዊ መብት ጥሰትን እንዲሁም የተደራጀ ሌብነትን ከስሩ ነቅሎ ለመጣልና በዜጎች ላይ አሰቃቂ ተግባራትን ሲፈፅም የነበረ እጅ እንዲሰበሰብ ብቻ ሳይሆን ለሰራው ጥፋት ተጠያቂ እንዲሆን በእጃቸው ካቴና በማስገባት ህግ ፊት ማቆም ጀምረናል» ሲል ፓርቲዉ በመግለጫዉ አክሎበታል። ይህን «አሰቃቂ» ርምጃ የሚወስዱት ላይ ክልሉ ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመሆን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን የኦሮምያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ምክትል ሃላፊዉ አቶ ዴሬሳ ለDW ተናግረዋል።

DW አስተያየታቸውን የጠየቃቸው በአምቦ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሞኔኑስ ሁንዳራ ገላታ መግለጫዉ ወቅታዊውን ሁኔታ ያገናዘበ አይደለም ሲሉ ለDW ተናግረዋል። አቶ ሞኔኑስ፥«ምክንያቱም በኦሮሚያ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ የኦሮሞ ህዝብ መፈናቀል ከአራት ወራት በላይ ጀምሮ ሳያቋርጥ ጠንክሮ ቀጥለዋል። ብዙ ግድያና የሰበአዊ መብቶች ጥሰት ኢየተፈፀመ ይገኛል። ይህም በተለያዩ መንገዶች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ አይን ዉስጥ እንዳይገባ ስደበቅ ነበር። በተለያዩ መንገድ የክልሉ ነዋርዎች ብቻ ነዉ ጉዳዩን አስመልክቶ ስወተዉቱ የነበሩት።»

ይሁን እንጅ የኦዲፒ የአቋም መግለጫ ተፈፃሚነት ላይ ሙሉ እምነት የለንም የሚሉም አሉ። በአምቦ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሞኔኑስ ሁንዳራ ጋላታ አንዱ ናቸዉ። መግለጫዉ ኦሮሚያና የኦሮሞ ህዝብ ያለበትን በደንብ አይገልፅም፣ ምክንያቱም ችግሩ በዚህ መንገድ ይፈታል የሚል የለም ሲሉ አቶ ሞኔኑስ ገልጸዋል። አቶ ሞኔኑስ፥ «አሁን በክልሉ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ ለሚፈፀሙት ጥቃቶች በሌሎች ሃይሎች ላይ ነዉ የክልሉ መንግስት ጣት ኢየቀሰረ ያለዉ። ይህም ባለፉት አምስት፣ ስድስት ወራት ሲናገር ከነበረዉ ጋር ተመሳሳይ ነዉ። መንግስት ለህዝብ ጆሮ የሚጥም ነገር ከመናገር ዉጭ የያዘዉን አቋም ወደ ስራ ሲለዉጥ አላየንም። ይህም ህዝብን ማታለልና ችግሩን አሳንሶ ማየት ይመስለኛል።»

የኦሮምያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፋ ህዝቡ ላይ እንዲህ አይነቱ ጥርጣሬ ማደሩ መንግስታቸዉ እንደምረዳ ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኮሚቴ ዉሳኔ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ያሉት አቶ ዴሬሳ ሆኖም የሚሰሩ ስራዎችን ዝርዝር ማንሳት እንደማይችሉ ለDW ገልፀዋል።

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE