እኛ መንግስቱ ኃይለማርያምን አስጠልለነው እንጁ ደብቀነው አይደለም ያለነው – የዚምባብዌው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

Zimbabwe Willing to Extradite Mengistu, Vows to Investigate How Late Rwandan Fugitive Mpiranya ‘Evaded Capture for Years’

የዚምባብዌው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀገራቸው ኮ/ል መንግስቱ ሀይለማርያምን ለኢትዮጵያ አሳልፋ ልትሰጥ እንደምትችል ጠቆሙ!
ሚኒስትሩ ፍሬዴሪክ ሻቫ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ላይ “የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የዚምባብዌ መንግስትን ቀርቦ ጥያቄ ካቀረበ አስፈላጊው እርምጃ ተወስዶ ተገቢው ጥያቄ መልስ ያገኛል” ብለዋል።
አክለውም “እኛ መንግስቱን አስጠልለነው እንጁ ደብቀነው አይደለም ያለነው” ብለዋል

Zimbabwe’s Foreign Affairs Minister Ambassador Frederick Shava has given the clearest sign ever that Harare is ready to extradite Ethiopian genocide fugitive and former President, Mengistu Haile Mariam. In an exclusive interview with VOA Zimbabwe, Shava said, “If the people of Ethiopia approach the government of Zimbabwe, appropriate steps will be taken by the Government of Zimbabwe in response to the request, to the legitimate request from the government of Ethiopia.”

ከዚህ በፊት የነበሩ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በዚህ ጉዳይ ዙርያ ሲጠየቁ መልሳቸው “በፍፁም አናረገውም” ነበር።
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በነበራቸው የመጀመርያ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የኮ/ል መንግስቱን ጉዳይ አንስቼ ነበር።
“በይቅርታ ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ እድል ይኖር ይሆን?” ብዬ ለጠየቅኩት ጥያቄ ሲመልሱ “ኮ/ል መንግስቱ የተከሰሱበት እና ፍርድ የተሰጣቸው ይቅርታ በማያሰጥ ከባድ ወንጀል ነው፣ ስለዚህ ህግ ካልተቀየረ በቀር ይህ አሁን ላይ የሚቻል አይደለም” ብለው ነበር።
(ሙሉ ዜናውን ለማንበብ –  https://www.voazimbabwe.com/a/6577243.html