ካሜሮን የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነቷ ተሰረዘ

የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ በካሜሮን አይካሄድም–ካፍ
እ.አ.አ አቆጣጠር የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ በካሜሮን እንደማይካሄድ ካፍ በዛሬው ዕለት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ካሜሮን በሰኔ ወር ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ በቂ ዝግጅት ባለማድረጓ ከአዘጋጅነት መሰረዟን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ካፍ አስታውቋል፡፡

አዲስ አዘጋጅ ሀገር በያዝነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ ይፋ እንደሚሆን የካፍ ፕሬዝዳን አህመድ አህመድ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE