እስካፍንጫው የታጠቀ ሰራዊት የሰባት ዓመት ልጄን አባትሽን አሳይን ብለው አስፈራርተዋል – ፋኖ አስረስ ማረ ዳምጤ

መንግስት በፋኖ ላይ የከፈተው የማጥቃት ዘመቻ የቀጠለ ሲሆን የፋኖ መሪዎችን ሲያጣ ሕፃናት ልጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ማስፈራራትና ማሰር ጀምሯል። ፋኖ አስረስ ማረ ዳምጤ ቤተሰቡ ያጋጠመውን እንደሚከተለው አስፍሯል።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዶ/ር ይልቃል ከፋለ ገዳይ ቡድን ከትላንት 8:00 ሰዓት ጀምሮ ቤቴን እንደከበበ ነው። ቤት ውስጥ የነበሩ ሁለት እህቶቸን ትላንት 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ አስሯቸው ውሏል።
ከዚህም የከፋ ነገር ስለምጠብቅ ነገሩ አልገረመኝም። ሆኖም እስካፍንጫው የታጠቀ የፈሪ ተላላኪ የሰባት ዓመት ልጀን አባትሽን አሳይን ብለው ማስፈራራታቸውን ስሰማ ለኋላ ቀርነታቸው ከልቤ አዘንኩ።
ፅዮንሻ አይዞሽ ያንች ብቻ ሳይሆን የብዙ ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ ነው።
ሁሉም የፋኖ አባል ካልተሰላ ግጭት እና መስዋዕትነት ራሱን አርቆ እንዲጠብቅ እመክራለሁ።