ልማት ባንክ ለ34 ሺሕ ሠልጣኞች 20 ቢሊዮን ብር ብድር አዘጋጀ

ልማት ባንክ ለ34 ሺሕ ሠልጣኞች 20 ቢሊዮን ብር ብድር አዘጋጀ

ባንኩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ብድር ወስደው ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ ከግንቦት 1 እስከ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚቆይ ሥልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን፣ በሥልጠናውም 34,000 ሠልጣኞች እንደሚሳተፉ የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) ገልጸዋል። ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ሥልጠና በ20 ከተሞችና በ32 ማዕከላት በመላ አገሪቱ ለሦስተኛ ጊዜ የሚሰጥ መሆኑን አክለዋል።