የልማት ድርጅቶች መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በዱቤ እንዲያስገቡ ተፈቀደላቸው

የልማት ድርጅቶች መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በዱቤ እንዲያስገቡ ተፈቀደላቸው

እየከፋ የመጣውን የዋጋ ግሽበት ለማርገብና ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ለመቀነስ መንግሥት መሠረታዊ ፍጆታዎች በዱቤ ከውጭ እንዲገቡ መፍቀዱን አስታወቀ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ስኳር፣ ዘይትና ስንዴን በዱቤ ወይም ዲፈርድ ሌተር ኦፍ ክሬዲት አሠራርን በመጠቀም ማስገባት ተፈቅዷል፡፡